የሚፈለጉ
ፍትህ የሚያመጣ መረጃ…

ያሲን አል ሱሪ

እስከ $10 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚደርስ ወሮታ

እዝዲን አብዴል አዚዝ ካሊል ፤ የበለጠውን በተለምዶ ያሲን አል- ሱሪ ተብሎ የሚታወቀው በኢራን አንጋፋ የአልቃይዳ አባል ነው። ያሲን አል- ሱሪ በታህሳስ 2011 ፤ ወሮታ ለፍትህ የ$10 ሚሊዮን ማስታወቂያ ከወጣ በኋላ በኢራን ባለሥልጣኖች ተይዞ ነበረ ፤ ነገር ግን እርሱ የAQ ኢራን መረብ መሪነቱን ጀምሮ ነበረ።

በኢራን የአልቃይዳ ኃላፊ በመሆኑ ያሲን አል- ሱሪ ልምድ ያላቸውን ሠራተኞችንና መሪዎችን ከፓኪስታን ወደ ሶሪያ ለማስተላለፍ ፤ በቱርክ በኩል አድርገው አዲስ ተመልመዮች ወደ ሶሪያ የሚገቡበትን መንገዶች በማስተካከልና በማደራጀት ፤ እና የአልቃይዳ የውጭ ሠራተኞችን ወደ ምዕራብ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ በመርዳት የአልቃይዳ ጥረቶችን ለመቆጣጠር ኃላፊነት ነበረው።

አል ሱሪ ገንዘብና ምልምሎችን ከመላው መካከለኛ ምሥራቅ መልምሎ ወደ ኢራን፣ከዚያም የአልቀይዳን አንጋፋ የአመራር አካላት ለመደገፍ ወደ ፓኪስታን ይሰዳል። የኢራን ባለሥልጣኖች ከአልሱሪ ጋር ግንኙነታቸውን ጠብቀው ከ2005 ጀምሮ በኢራን ድንበሮች እንዲሰራ ዘንድ ፈቅደውታል።

አል ሱሪ ለአልቀይዳ ምልምሎችን ከባህረ ሰላጤ በኢራን በኩል አድርጎ ወደ ፓኪስታንና አፍጋኒስታን እንዲንቀሳቀሱ ያመቻቻል። እርሱም ለአልቀይዳ ጠቃሚ ገንዘብ ሰብሳቢ ነው እናም ከለጋሾችና ገንዘብ ከሚያዋጡት በመለው ባህረ ሰላጤ ሰብስቦአል። አል ሱኒ በርካታ ገንዘብ በኢራን በኩል አድርጎ በአፍጋኒስታንና በኢራቅ ላለው የአልቀይዳ አመራር ያስተላልፋል።

ከኢራን መንግሥት ጋር በመሆን፣አል ሱኒ የአልቀይዳ ሠራተኞች ከኢራን እስር ቤቶች እንዲወጡ ዘንድ ያመቻቻል። የአልቀይዳ ሠራተኞች ሲፈቱ፣ የኢራን መንግሥት ጉዞአቸውን ወደ ፓኪስታን ወደሚያቻቸው ወደ አል ሱሪ ያስተላልፋቸዋል።

ተጨማሪ ፎቶዎች

ያሲን አል ሱሪ