የሚፈለጉ
ፍትህ የሚያመጣ መረጃ…

ያህያ ሀቃኒ

እስከ $5 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚደርስ ወሮታ

ያህያ ሀቃኒ ፣ በቡድኑ ወታደራዊ ፣ በገንዘብ ፣ እና በፕሮፖጋንዳ ተግባሮች በቅርበት ተሳታፊ የሆነ የሀቃኒ አውታር አንጋፋ አባል ነው። እጅግ አንጋፋ መሪዎች ስራጁዲን ሀቃኒ(የያህያ አማች)ከሊል ሀቃኒ ፣ እና ባሩዲን ሀቃኒ (የሞቱት) ሲጠፋ ስራጁዲን ሀቃኒ ያህያ በርግጥ የቡድኑ መሪ ሆኖ አገልግሎአል። ያህያ ደግሞ የሀቃኒ አውታር የእቅድና የዝግጅት ክፍል ሠራተኛ(ሎጂስትሺያን)ሆኖ ሠርቶአል እና አሁኑ የሞተው የሀቃኒ አውታር አዛዥ ሳንጊን ዛድራን እና የ የሀቃኒ አውታር የአጥፍቶ ጠፊ ተግባሮች ኃላፊ ፣ አብዱል ራሁፍ ዛኪር የበታች ሆኖ ጨምሮ ለሀቃኒ አዛዦች ገንዘብ የማሰባሰብ ሥራ አመቻችቶአል። ያያ ደግሞ የስራጁዲን ሀቃኒ የአረብኛ አስተርጓሚና ተላላኪ ሆኖ ሰርቶአል።

ያህያ የሀቃኒ አውታር ጥቃቶችንና ሌሎች ተግባሮችን በመደገፍ በርካታ የማመቻቻ ድርጊቶች ፈጽሞአል። እርሱም በ2013 መጀመሪያ ፣ ለሀቃኒ አውታር ተዋጊዎች ገንዘብ አመቻችቶአል። ያህያ ደግሞ በ2013 መጀመሪያ ፣ ለአንጋፋው ሀቃኒ አውታር መሪ ለከሊል ሀቃኒ ከተባበሩት አረብ ኢምሬትስ የዕቃዎችን ማስተላለፍ ሥራ አስተባብሮአል። በ2012 ፣ ያህያ በቤት ውስጥ/በድብቅ የተሰሩ የሚፈነዱ መሳሪያዎችን (IEDs)ና የመገናኛዎችን መሳሪያ ማከፋፈያን አስተባብሮአል ፣ እና በሎጋር አውራጃ ፣ አፍጋኒስታን በCoalition Forward የሥራ ማዕከል የተፈጸመውንና ፣ አሥራ አንድ የአፍጋኒስታን ሲቪሎችን ጨምሮ ቆስለው ፣ አሥራ ሦሥት ሰዎች የተገደሉበትን የሀቃኒ አውታር ጥቃት የነሀሴ 7 ቀን 2012 ዝግጅቶችን ከልሶአል። እስከ 2011 ድረስ ያህያ ከስራጁዲን ሀቃኒ ወደ ሀቃኒ አውታር አዛዦች ለድርጊቶች አስተላልፎአል።

ያህያ አንዳንድ ጊዜ በሀቃኒ አውታርና በአልቃይዳ መካከል እንደ አገናኝ ሆኖ ያገለግላል እና ቢያንስ ከመካከለኛ -2009 ጀምሮ ከአልቃይዳ ጋር ግኑኝቶቹን ቀጥሎአል። በዚህ ሚና ፣ ያህያ በአካባቢው ለአልቃይዳ አባላት ለግል ወጪዎቻቸው ገንዘብ ሰጥቶአል። እርሱም ከመካከለኛ -2009 ጀምሮ አረቦችን ፣ ኡዝቤኮችን ፣ እና ቼቼኖችን ጨምሮ ለውጭ ተዋጊዎች የሀቃኒ አውታር ዋና አገናኝ ሆኖ ሰርቶአል።

ያህያ ደግሞ የሀቃኒ አውታርና የታሊባን ሚዲያና ፕሮፖጋንዳ ተግባሮች አካሄዶአል እና መርቶአል። ከ2012 መጀመሪያ ጀምሮ ፣ ያህያ የሠራውን ያታሊባን ፕሮፖጋንዳ ቪዲዮ የመጨረሻ ፈቃድ ለማግኘት ከስራጁዲን ሀቃኒ ጋር ተገናኝቶአል። ያህያ በአፍጋኒስታን ከሚዋጉ ተዋጊዎች ያገኘውን ቪዲዮ በሀቃኒ አውታር ማድራሳ በእስቱዲዮ ኤዲት ባደረገ ጊዜ ቢያንስ ከ2009 ጀምሮ በሀቃኒ አውታር ሚዲያ ድርጊቶች ሰርቶአል። ከ2011 መጨረሻ አካባቢ ጀምሮ ፣ ከስራጁዲን ሀቃኒ ወይም ከስራጁዲን ምትኮች አንዱ ያህያ ለሀቃኒ አውታር ሚዲያ ወጪዎች ገንዘብ አግኝቶአል።

የአሜሪካ የዉጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በየካቲት 5 ቀን 2014 በሥራ አፈጻጸም መመሪያ 13224 መሠረት ያህያ ሀቃኒን የዓለም አቀፍ አሸባሪ አድርጎ ፈርጆታል።

የ-----ተጨማሪ ፎቶ

ተጨማሪ ፎቶዎች ያህያ ሀቃኒ
ተጨማሪ ፎቶዎች ያህያ ሀቃኒ