የሽብርተኝነት ድርጊቶች
መረጃ በ ...

በአለም የንግድ ማዕከል ላይ የተፈፀመ የቦምብ ጥቃት

ኒው ዮርክ ከተማ እንደ አ.አ.አ | የካቲት 26፣ 1993

የካቲት 26 ቀን 1993 – በኒውዮርክ በሚገኘው የአለም የንግድ ማእከል አንደኛው ሕንጻ ስር በመኪና ላይ የተጠመደ ቦምብ ፈንድቶ ነበር፡፡ የዚህ የ1500 ፓውንድ ቦምብ ፍንዳታ አላማም ሕንጻ አንድን በመምታት ሁለቱን ሕንጻዎች እንዲወድሙ በማድረግ በሼዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ለመግደል ነበር፡፡ ይህ የቦምብ ፍንዳታ አንዱንም ሕንጻ ባያወድምም ስድስት ሰዎችን ገድሎ ከአንድ ሺህ የሚበልጡ ሰዎችን በማቁሰል በብዙ ሚሊዮን ዶላር በሚገመት የንብረት ጉዳት አድርሷል፡፡.

ይህ ጥቃት ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት ባላቸው ብዙ ሰዎች የታቀደ ሲሆን አብዱልራህማን ያሲን፣ ራምዚ ዮሱፍ እና በርካታ ሌሎች ሰዎች ተሳትፈውበታል፡፡ ዘመቻውን በገንዘብ ያገዘው የራምዚ ዮሱፍ አጎት የሆነው ካሊድ መሃመድ ሲሆን የአልቃይዳ ከፍተኛ አባል ነው፡፡ አቀናባሪውን ራምዚ ዮሴፍን ጨምሮ ከዚህ ጥቃት ጋር ግንኙነት ያላቸው ስድስት ሰዎች ተከሰ ዋል፡፡.

ወሮታ ለፍትህ ፕሮግራም ለዚህ ጥቃት ተጠያቂ የሆኑ ሰዎችን ወደ ፍትህ ለማቅረብ የሚያስችሉ መረጃዎችን ለሚሠጡ ሰዎች እስከ 1 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚደርስ ወሮታ ያበረክታል፡፡.