የሽብርተኝነት ድርጊቶች
መረጃ በ ...

ቲ ደብሊዩብ ኤ የበረራ ቁጥር 847 ጠለፋ

ቤይሩት ሊባኖስ እንደ አ.አ. | ሰኔ 14፣1985

በሰኔ 14፣1985 ከሂዝቦላ ጋር ግንኙነት ያላቸው አሸባሪዎች ከአቴንስ ወደ ሮም፣ኢጣሊያ በመብረር ላይ የነበረን TWA Flight የበረራ ቁጥሩ 847 የሆነ አውሮፕላን ጠልፈዋል፡፡ አሸባሪዎቹ መጀመሪያ አውሮፕላኑ በረራውን ወደ ቤይሩት እንዲያዞር በማስገደድ ነዳጅ ለማግኘት በልዋጩ ብዙ መንገደኞችን ለቀዋል፡፡ ከዚያም ወደ አልጀርስ በማምራት አውሮፕላኑ ወደ ቤሩት ከመመለሱ በፊት ሌሎች ተጨማሪ መንገደኞች ተለቀዋል፡፡

በቤሩት የአሜሪካ ባህር ሃይል ጠላቂወታደር የሆነውን ሮበርት ስቲተምን ከአሸባሪዎች ለይተው አውቀዋል፡፡ አሸባሪዎቹ ታጋቹን በመደብደብ ገድለው ሬሳውን ሜዳው ላይ ጥለውታል፡፡ አውሮፕላኑ ተጨማሪ 65 ሰዎች ወደ ተለቀቁበት ወደ አልጀርስ ከመመለሱ በፊት ቤሩት ውስጥ ሌሎች ተጨማሪ 12 መሳሪያ የታጠቁ ሰዎች ወደ አውሮፕላኑ ገብተዋል፡፡

በመጨረሻም፣ በረራው በድጋሚ ወደ ቤሩት ተመልሶ፣እስከ ሰኔ 30 ፣ ቀሪዎቹ መንገደኞች ወደ ሶሪያ እስከሚሄዱ ድረስ ቆይተዋል፡፡ ሶሪያ ውስጥ በአሜሪካ አየር ሃይል አውሮፕላን ተጭነው ወደ ምእራብ ጀርመን ተጓጉዘዋል:: ለዚህ ጥቃት ተጠያቂ የሆኑት አሸባሪዎች መካከል አሊ አትዋ፣ ሀሰን ኢዛ አል ዲን፣ መሃመድ አሊ ሐማዲ፣ እና በርካታ ሌሎችም ይገኙበታል፡፡

ወሮታ ለፍትህ ፕሮግራም ለዚህ ጥቃት ተጠያቂ የሆኑ ሰዎችን ወደ ፍትህ ለማቅረብ የሚያስችሉ መረጃዎችን ለሚሠጡ ሰዎች እስከ 1 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚደርስ ወሮታ ያበረክታል፡፡.