የሽብርተኝነት ድርጊቶች
መረጃ በ ...

የኬቪን እስኮት ሱታይ አፈና

በሰኔ 20 ቀን 2013፣ የአሜሪካ ዜጋ የነበረው ኬቪን እስኮት ሱታይ በኮሎምቢያ አብዮታዊ ሰራዊት (Revolutionary Armed Forces of Colombia (FARC)) በኤል ሬቶርኖ ፣ ኮሎምቢያ ታፍኖአል። ሱታይ፣ የቀድሜ የአሜሪካ ጦር አባል ፣ በበርካታ ማዕከላዊና ደቡብ አሜሪካ አገሮች ጎብኚ ሆኖ በረጅም ጉዞ ላይ ነበረ ።

በሀምሌ 19 ቀን 2013 ፣ FARC ለሱታይን መታፈን ኃላፊነት መውሰዱንና በቅንነት ለመልቀቅ ፍላጎት እንዳለው ለህዝብ ይፋ ማስታወቂያ አውጥቶአል። ዳሩ ግን ፣ ሱታይ በጉያቪያሬ ክፍል ለኮሎምቢያ ፣ ኩባ ፣ እና ኖርዌይ ፣ እና ለዓለም አቀፍ የቀይ መስቀል ማህበር አባላት ልዑካን ቡድን እስከተሰጠ ጊዜ ድረስ ሱታይ እስከ ጥቅምት 27 ፣ 2013 ድረስ አልተለቀቀም። ከዚያ ቦታ ፣ ሱታይ ለአሜሪካ መንግሥት ባለሥልጣናት በቦጎታ ፣ኮሎምቢያ ተሰጥቶ፣ ወደ አሜሪካ በሮአል።

ወሮታ ለፍትህ መርሃ ግብር ፣ ለዚህ ጥቃት ተጠያቂ የሆኑትን ለፍትህ ለሚያቀርብ መረጃ እስከ $3 ሚሊዮን ይሰጣል።