የሚፈለጉ
ፍትህ የሚያመጣ መረጃ…

ሳሚ ጃስም ሙሃመድ አል ጀቡሪ

እስከ $5 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚደርስ ወሮታ

ሳሚ ጃስም ሙሃመድ አል ጀቡሪ፣ ደግሞ ሃጂ ሃሚድ የሚባለው፣ የኢራቅና ሶሪያ እስላማዊ መንግሥት (ISIS) አንጋፋ መሪ ነው እና ከISIS በፊት ለነበረው ድርጅት ለኢራቅ አልቃይዳ (AQI) የውርስ አባል ነው፡፡ ሙሃመድ አል ጀቡሪ ለ ISIS የአሸባሪነት ውጊያዎች ፋይናንሶችን በማስተዳደር ቁልፍ ሰው ነው፡፡

በ2014 በደቡብ ሞሱል የISIS ምክትል ሆኖ እየሰራ፣ ከዘይት፣ ጋዝ፣ የጥንት እቃዎች፣ እና ማዕድኖች ህገወጥ ሽያጮች የቡድኑን የገንዘብ ምንጭ የሆኑትን ድርጊቶችን በመቆጣጠር የISIS የገነዘብ ሚንስቴር በሆነ ተመጣጠኝ ማዕረግ እንደሰራ ይነገራል፡፡

የአሜሪካ የገንዘብ ሚንስቴር፣ ለአሸባሪዎችና ለአሸባሪዎች ወይም ለሽብርተኝነት ተግባሮች ድጋፍ በሚሰጡ ላይ የገንዘብ ማእቀብ በሚበይነው በሥራ መመሪያ ትዕዛዝ 13224 መሰረት እርሱ አለማቀፋዊ አሸባሪ እንደሆነ ፈርጆታል፡፡

በሰኔ 2014፣ ዳእኤሽ በመባል ደግሞ የሚታወቀው ISIS የእራቂና የሶሪያ ከፊሎቹን ተቆጣጥሮ እስላማዊ “ካልፌት” ብሎ እራሱ ሰይሞት አልባዳዲን “ካሊፍ” ብሎ ሰይሞታል፡፡ በቅርብ አመታት ወስጥ፣ ISIS የጂሃድስት ቡድኖችን ድጋፍ አግኝቶአል እና በመላው አለም ላይ ጥቃቶችን እንዲያካሄዱ የግለሰቦችን አእምሮ ለውጦአል፡፡

ይህ ወሮታ ከ ISIS ጋር በምንዋጋበት ጊዜ ጠቃሚ ነው፡፡ ISIS በጦር ሜዳ በመሸነፉ፣ ISIS ን ለማሸነፍ የሚዋጋው አለማቀፋዊ የአገሮች ህብረት የ ISISን ቅሬታዎች ለማጥፋትና አለማቀፋዊ ምኞቱን ለመቀልበሰ ለመቀጠል እንዲችል ዘንድ የቡድኑን መሪዎች ለይቶ ለማወቅና ለማግኘት እኛ ቆርጠን ተነስተናል፡፡

የተጨማሪ ፎቶ

ሳሚ ጃስም ሙሃመድ አል ጀቡሪ