የሚፈለጉ
ፍትህ የሚያመጣ መረጃ…

ሰይፍ አል አደል

እስከ $10 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚደርስ ወሮታ

አል – አድል የአልቃይዳ አንጋፋ መሪና “የመጅሊስ አል- ሹራ” ፣ የአልቃይዳ አመራር ምክር ቤት አባል ነው ፡፡አል – አድል የአልቃይዳን ተወታደራዊ ኮሚቴን ይመራል፡፡

አል – አድል፣ በደሬሳለም፣ ታንዛኒያ እና በናይሮቢ፣ ኬንያ፣ በነሀሴ 7 ቀን 1998 ፣ በአሜሪካ ኤምባሲዎች ላይ ለደረሱት የቦምብ ጥቃቶች በነበረው ሚና፣ በታህሳስ 1998 በፌዴራል ጠቅላይ የፍርድ ጁሪ ክስ ተመስርቶበታል፡፡ ጥቃቶቹ 224 ሲቪሎችን ገድሎ ከ5,000 በላይ የሆኑትን ሌሎችን አቁስሎአል፡፡

እርሱም ከግብጽ የአገር ውስጥ ሚኒስቴር የግድያ ሙከራ በኋላ በ1987 ከሌሎች የጸረ መንግሥት ተዋጊዎች ጋር እስከታሰረ ድረስ በግብጽ የልዩ ሃይሎች ውስጥ ሌተናንት ኮሎኔል ነበረ

በ1990 መጀመሪያ፣ አል አድል እና ሌላ የአልቃይዳ ተዋጊዎች፣ አፍጋኒስታን፣ ፓኪስታንና ሱዳን፣ የግብጽ እስላማዊ ጂሃድ ጭምር ለአልቃይዳና ከርሱ ጋር ተዛማጅ ለሆኑ ቡድኖች፣ በተለያዩ አገሮች የውትድርናና የእንቴልጄንስ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡

በ1992ና 1993፣ እርሱና አብዱላሂ ለአልቃይዳ ተዋጊዎች እንዲሁም በ Operation Restore Hope ወቅት ከአሜሪካ የጦር ሃይሎች ጋር ለተዋጉት ለሶማሊያ የጎሳ ሰዎች የውትድርና ሥልጠና ሰጥቶአል፡፡

እርሱም፣ በደሬሳለም፣ ታንዛኒያ እና በናይሮቢ፣ ኬንያ፣ በነሀሴ 7 ቀን 1998 ፣ በአሜሪካ ኤምባሲዎች ላይ ለደረሱት የቦምብ ጥቃቶች በነበረው ሚና፣ በታህሳስ 1998 በፌዴራል ጠቅላይ የፍርድ ጁሪ ክስ ተመስርቶበታል፡፡

ከደረሱት የቦምብ ጥቃቶች በኋላ፣ አል – አድል ወደ ደቡብ ምስራቅ ኢራን ሄዶአል እና በ ኢራን Islamic Revolutionary Guard Corps (IRGC) ጥበቃ ሥር ኖሮአል፡፡ በሚያዚያ 2003 የኢራን ባለሥልጣናት እርሱን፣ አብዱላሂንና ሌሎች የአልቃይዳ መሪዎችን የቤት ውስጥ እስረኞች አድርጎአቸዋል፡፡

በመስከረም 2015፣ በየመኑ አልቃይዳ በታገተው የኢራን ዲፕሎማት ልዋጭ አል – አድልና ሌሎች የአልቃይዳ መሪዎች ከኢራን እስር ቤት ተለቀቁ፡፡

አል – አድል ደግሞ፣ በኋላ ISIL ለሆነው ለኢራቁ አልቃይዳ መሥራች ለአቡ ሙሳብ አል ዛርካዊ አንጋፋ ምክትል ነበረ፡፡

የተጨማሪ ፎቶ

English AAA and SaA PDF