የሽብርተኝነት ድርጊቶች
መረጃ በ ...

በመኖሪያ ግቢዎች ላይ የተፈፀ ሙ የቦንብ ጥቃቶች

ሪያድ፣ ሳኡዲ አረብያ | እ.አ.አ. ግንቦት 12፣ 2003

ግንቦት 12 ቀን 2003 በሳኡዲ አረብያ ሪያድ በ3 የተለያዩ የመኖሪያ ግቢዎች ላይ አራት በመኪና ላይ የተጠመዱ ቦምቦች ፈንድተዋል፡፡ ይህ ፍንዳታ ያነጣጠረው በምዕራባውያን ላይ በተለይ በአሜሪካና በእንግሊዝ ዜጎች ላይ ነበር፡፡ ጥቃቱ 8 አሜሪካውያንን ጨምሮ 20 ሰዎችን የገደለ ሲሆን ወደ 200 የሚጠጉ ሰዎችን አቁስሏል፡፡ ጥቃቱን ያቀናበረው እና ያስተባበረው አልቃኢዳ ነበር፡፡.

ወሮታ ለፍትህ ፕሮግራም ለነዚህ ጥቃቶች ተጠያቂ የሆኑ ሰዎችን ወደ ፍትህ ለማቅረብ የሚያስችሉ መረጃዎችን ለሚሰጡ ሰዎች እስከ 5 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚደርስ ወሮታ ያበረክታል፡፡ .