የተሳካ ታሪክ

ራምዚ አህመድ ዩሴፍ

ወንጀለኝነታቸው በፍርድ ቤት የተረጋገጠባቸው

ራምዚ አህመድ ዩሴፍ እ.አ.አ 1993 ውስጥ ለስድስት ሰዎች ሞትና ከሺ በላይ ቁስለኞች የሆኑበት በኒውዮርኩ የአለም ንግድ ማዕከል ላይ ለደረሰው የቦንብ ጥቃት በዋነኛ አቀናባሪነት ተጠያቂ የነበረ አሸባሪ ነው፡፡ ፍንዳታው በደረሰ በሰዓታት ጊዜ ውስጥ ራምዚ በአውሮፕላን ወደ ፓኪስታን አምልጧል፡፡

ዩሱፍ ውስብስብ የሽብር ሴራ ባደራጀበት ሀገር ፊሊፒንስ ውስጥ ብቅ አለ፡፡ ዩሱፍ ሊቀ ጳጳስ ፖል 2ኛ እ ኤ አ ጥር 14፣ 1995 ፊሊፒንስ ሲጎብኙ ለመግደልና ከጥቂት ቀናት በኋላም በእስያ በ12 የአሜሪካ የመንገደኞች አውሮፕላኖችን በቦንብ ለማፈንዳት አቅዶ ነበር፡፡ አጠቃላዩ ሴራ “ኦንላን ቦይንካ” ተብሎ ሲጠራ በአረብኛ ሲተረጎም የፍንዳታ ዘመቻ ወይም ቢግ ባንግ ዘመቻ በመባል ይታወቃል፡፡ ዩሱፍ የዚህ ዘመቻ ዋነኛ አቀነባሪ እንደነበር ግልጽ ሲሆን ነገር ግን የዘመቻው ሌሎች ቁልፍ ተዋናዮች ዋሊ ካን አሚን ሻህ፣ አብዱልሀኪም ሙራድ፣ ካሊድ ሼህ መሀመድ (የዩሱፍ አጎትና ከመስከረም 11 ጥቃት አቀናባሪዎች ቀንደኛው) እና ሀምባሊ – ሁሉም ቃለ መሃላ የፈፀሙ የአልቃኢዳ አባላት ይገኙበታል፡፡

የአጠቃላይ ሴራ አካል በመሆን፣ ጥር 21 እና 22፣1995 እያንዳንዱ በረራ መጀመሪያ ማረፊያዎች በምስራቅና ደቡብ ምስራቅ ኤስያ ሲያርፉ በ12 የአሜሪካ የመንገደኞች አውሮፕላኖች ላይ አምስት አሸባሪዎች ቦምብ አጥምደው በመውረድ አውሮፕላኖቹ ሠላማዊ ውቅያኖስ ላይ እየበረሩ እያሉ እንዲፈነዱ ያደርጋሉ፡፡ አምስቱም አሸባሪዎች 12 አውሮፕላኖች ላይ ቦምብ የማጥመድ ሥራን ይሰራሉ፡፡ በዚህ እቅድ ሊሞቱ ይችላሉ የተባሉት ሰዎች ግምት 4000 ነበር፡፡

መልካም እድል ሆኖ፣ ዩሴፍና ተባባሪዎቹ ውድቀት ያስከተለባቸውን ቸልተኝነት አሳዩ፡፡ ጥር 6፣ 1995 ላይ ከአፓርታማቸው መስኮት አፈትልኮ የወጣ ጭስ በኬሚካል ውህድ ሲፈጠር ሙራድና የሱፍ ማኒላ ውስጥ ካለው አፓርታማ ሸሽተው ይወጣሉ፡፡ ከዚያም ሙራድ ወደ አፓርታማው ተመልሶ ላፕቶፕ ኮምፒውተሩንና ሌሎች በወንጀል የሚያስጠይቁ መረጃዎችን እንዲያወጣ የሱፍ በጠየቀው መሠረት ወደ አፓርታማው ሲመለስ ቀድሞ ከደረሰው የፖሊስ ኃይል ጋር ሊጋፈጥ ችሏል፡፡ የሱፍም፣ ሙራድ በፖሊስ እንደተያዘ በመገንዘቡ ወደ ፓኪስታን ሊሸሽ ችሏል፡፡

እ ኤ አ የካቲት 1995 ውስጥ የወለፍን የሽልማት ማስታወቂያ ተመልክቶ የተበረታታ መረጃ ሰጭ ፓኪስታን ኢስላማባድ ውስጥ ወደሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ በመቅረብ የሱፍ የሚገኝበትን ቦታ በተመለከተ መረጃ ሊሰጥ ችሏል፡፡ ከዚያም በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዲፕሎማቲክ ደህንነት ሠራተኞች የሚረዱ የፓኪስታን ባለስልጣናት የሱፍን በኢስላማባድ፣ ፓኪስታን ውስጥ በቁጥጥር ሥር አውለው ወደ ዩናይትድ ስቴትስ እንዲላክ አድርገዋል፡፡ የሱፍ አሁን ኮሎራዶ ውስጥ ታስሮ ይገኛል፡፡ በኦፕላን ቦይንካ ዘመቻ የተሳተፉ ሌሎች አራት ዋነኛ ተዋናዮቸም በቁጥጥር ሥር ውለዋል፡፡