የሚፈለጉ
ፍትህ የሚያመጣ መረጃ…

ካሲም አል-ሪሚ

እስከ $10 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚደርስ ወሮታ

ቃሲም አል-ሪሚ፣ ለአልቃኢዳ መሪ አይማን አልዘዋሃሪ ታማኝነቱን ካረጋገጠ በኋላ፣ እ.ኤ.አ. በሰኔ 2015 ውስጥ የAQAP እምር ሆኖ ተሰይሞአል፣ እና በዩናይትድ ስቴትስ ላይ እንደገና ጥቃቶች እንዲፈፅሙ ጥሪ አቅርቧል፡፡ አል-ሪሚ በ1990ዎቹ በአፍጋኒስታን የአልቃኢዳ ካምፕ አሸባሪዎችን አሠለጠነ፣ እና ከዚያም ወደ የመን ተመልሶ የAQAP ወታደራዊ አዛዥ ሆነ፡፡ በ2005 በየመን የአሜሪካን አምባሳደር ለመግደል በማሴሩ የአምስት ዓመት እስራት ተፈርዶበታል፣ እና በ2006 አመለጠ፡፡ በመስከረም 2008 በሰናአ በአሜሪካ ኤምባሲ ላይ ተከስቶ 10 የየመን ጠባቂዎችን፣ አራት ሰላማዊ ሰዎችን እና ስድስት አሸባሪዎችን ከገደለው ጥቃት ጋር አል-ሪሚ ተያይዞአል፡፡ ወደ አሜሪካ በሚጓዘው አውሮፕላን ላይ ከታህሳስ 2009 “የውስጥ ልብስ ቦምብ አፈንጂ” ከአጥፍቶ ማጥፋት ሙከራ ኡማር ፋሩክ አብዱልሙታላብ ጋር አል-ሪሚ ተያይዞአል፡፡ በየመን የአቢያን ግዛት የአልቃኢዳን ማሰልጠኛ ካምፕ በማንቀሳቀሱ እ.ኤ.አ በ2009፣ የየመን መንግሥት ከሶታል ፡፡

በግንቦት 7 ቀን 2017 ቪዲዮ ላይ፣ “ቀላል ” የሆኑ ጥቃቶችን እንዲያካሄዱ በምዕራባውያን አገሮች የሚኖሩ ደጋፊዎችን ወትዉቶአል፣ እና በኦርላንዶ ፍሎሪዳ በምሽት የዳንስ ክለብ ላይ 49 ሰዎችን በሰኔ ወር 2016 በጅምላ የገደለውን ኦማር ማቲንን አወድሶአል፡፡

በግንቦት 2010፣ የአሜሪካ የውጭ ጉዲይ ሚኒስቴር አል-ሪሚን በስራ ማስፈጸሚያ ትዕዛዝ 13224 አለምአቀፍ አሸባሪ እንደሆነ ፈርጆበታል፡፡ በግንቦት 2010 አል-ሪሚ ከአልቃኢዳ / አይሲሊ (al Qa’ida/ISIL (Qa’ida/ISIL)) ጋር የተቆራኙ ግለሰቦች ዝርዝር ውስጥ በተባበሩት መንግስታት (UN) 1267 የማእቀብ ኮሚቴ ውስጥ ተጨምሯል፡፡ ለአል-ሪም የመጀመሪያው የ5 ሚሊዮን ዶላር ወሮታ በጥቅምት 14 ቀን 2014 ተሰጥቶአል፡፡

የተጨማሪ ፎቶ

ካሲም አል-ሪሚ
al-Rimi and Batarfi English PDF
al-Rimi and Batarfi Arabic PDF
AQAP English PDF
AQAP Arabic PDF