የሽብርተኝነት ድርጊቶች
መረጃ በ ...

የፓን አ ም በረራ ቁ 73 ጠለፋ

ካራቺ ፓኪስታን | ነሐሴ 30፣ 1978 ዓ.ም. (እንደ አ.አ. መስከረም 5፣ 1986)

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴ ር ሁሉም የአቡኒዳል አሸባሪ ድርጅት አባላት እንደሆኑ የሚታመኑትን ዋዳውድ ሙሐመድ ሀፊዝ አል-ቱርኪን፣ ጀማል ሰኢድ አብዱል ራሒምን፣ ሙሐመድ አብዱላ ካሊል ሁሴን አር-ራያልንና ሙሐመድ አል-ሙናዋርን ለማግኘትና በቁጥጥር ሥር ለማዋል ወይም ለመክሰስ የሚያስችል መረጃ ለሚሰጥ ለያንዳንዱ መረጃ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መ/ቤት እስከ 5 ሚሊዮን ዶላር ድረስ ወሮታ መድቧል፡፡

በፓኪስታን ካራቺ ነሐሴ 30 ቀን 1978 ዓ.ም. (እንደ እ አ. አ. ሴፕቴምበር 5 ቀን 1986) ከጠዋቱ በግምት 12 ሰዓት ላይ በረራ ቁ 73 ፓን አም አውሮፕላን በመንደርደሪያ ላይ እያለ በአቡኒዳል ድርጅት አባላት ተጠለፈ፤ በአውሮፕላኑ ውስጥ በጠለፋው ወቅት 379 ተሳፋሪዎችና የበረራው ሠራተኞች ሲኖሩ ከእነዚህም ውስጥ ቢያንስ 78 የሚሆኑት የአሜሪካዊ ዜግነት ያላቸው ነበሩ፡፡ የበረራው ሠራተኞች አውሮፕላኑ እንዳይንቀሳቀስ አድርገው ሲያመልጡ ጠላፊዎቹ አውሮፕላኑን ተቆጣጥረው እነርሱንና ተሣፋሪዎቹን ወደ ቆጵሮስ የሚወስዳቸው የበረራ ቡድን እንዲቀርብላቸው ጥያቄ አቀረቡ፤ በጠለፋው ወቅት አንድ አሜሪካዊ ዜጋ በአውሮፕላኑ በራፍ ላይ ተገደለ፤ በጠለፋው ማክተሚያ ላይ ጠላፊዎች በተሣፋሪዎቹ ላይ ተኩስ ከፍተው 20 የሚሆኑ ተሳፋሪዎች ሲገደሉ ቢያንስ 100 የሚሆኑት ደግሞ ከፍተኛ የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል፡፡

በወቅቱ የፓኪስታን መንግሥት አራቱን ተጠርጣሪዎች እቦታው ላይ በቁጥጥር ሥር ያዋላቸው ሲሆን በኋላም ጥቃት እንዲደርስ የረዳውን አምስተኛውን ተጠርጣሪ ግለሰብ ይዟል፡፡ የወሮታ ክፍያ የተጣለባቸው አራቱን ግለሰቦች ጨምሮ አምስቱም በክስ ፍርዳቸውን ተቀብለው በፓኪስታን ወህኒ ቤት በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡

በመስከረም, 1984 ዓ.ም. (እአ.አ. ሴፕቴምበር, 2001) ዛይድ ሐሰን አብድ አል-ላቲፍ ሳፋሪኒ ከአምስቱ ተከሳሽ አሸባሪዎች አንዱ ሲሆን በፓኪስታን ባለሥልጣኖች ከእስር ተለቆ ነበር፡፡ ቆይቶም በኤፍ ቢ አይ በቁጥጥር ሥር ከዋለ በኋላ በ ዩኤስ (አሜሪካ) ፌደራል ፍርድ ቤት ክስ ቀርቦበታል፡፡ በታሕሳስ 7 ቀን 1996 ዓ.ም. (እ አ.አ. በዲሴምበር 16 ቀን 2003) ሳፋሪኒ በአሜሪካ የፍትህ ዋና መስሪያ ቤት መልስ እንዲሰጥበት ያቀረበለትን ሰምምነት ተቀብሎ ነበር፡፡ ግንቦት 5 1997 ዓ.ም. (እ አ.አ. በሜይ 13 2005) የ160 ዓመት እስራት ተፈርዶበታል፡፡

በጥር 2000 ዓ.ም. (እ አ.አ. በጃንዋሪ 2008) የወሮታ ክፍያ የተጣለባቸው እነዚህ አራት ጠላፊዎች በቁጥጥር ሥር ከነበሩበት የፓኪስታን እገታ እንደተለቀቁ መረጃዎች ያስረዳሉ፡፡ ዋዱድ ሙሐመድ ሀፊዝ አል-ቱርኪ፣ጀማል ሰኢድ አብዱል ራሒምን፣ሙሐመድ አብዱላ ካሊል ሁሴን አር-ራያልንና ሙሐመድ አል-ሙናዋር በአውሮፕላን ጠለፋና በሌሎች ወንጀሎች ውስጥ በነበሯችው ድርሻዎች መነሻ በኮሎምቢያ ዲስትሪክት ክስ የቀረበባቸዋ ሲሆን እስካሁንም አልተያዙም፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በአሸባሪነት ተግባር የሚፈለጉ የሚለውን ይመልከቱ

ዋዱድ ሙሐመድ ሀፊዝ አል-ቱርኪ

ሙሐመድ አሕመድ አል-ሙናዋር

ሙሐመድ አብዱላ ካሊል ሁሴን አር-ራሃያል

ጀማል ሳኢድ አብዱል ራሒም