የሽብርተኝነት ድርጊቶች
መረጃ በ ...

2008 የሙምባይ ጥቃት

ሙምባይ፣ ሕንድ | እ ኤ አ ከህዳር 26-29 ቀን 2008

ከህዳር 26 ቀን 2008 ጀምሮ እስከ ጥቅምት 29 ቀን 2008 ድረስ በፓኪስታናዊው የሽብርተኛ ድርጅት ላሽካር-ኤ-ታይባ (ሌት) (Lashkar-e-Tayyiba (LeT)) የሰለጠኑ አሥር አጥቂዎች በሙምባይ፣ ሕንድ ውስጥ ታጅ ማሃል ሆቴል፣ ኦቤሮእ ሆቴል፣ ዜ ሌፖርድ ካፌ፣ ናሪማን (ቻባድ) ቤት፣ እና ቻተራፓቲ ሺቫጅ ቴርሚናስ የባቡር ጣቢያ ጭምር በበርካታ ኢላማዎች ላይ የተቀናጁ ጥቃቶችን ያካሄዱ ሲሆን፣ በግምት 170 ሰዎችን ገድለዋል፡፡

በሶስት ቀን ጊዜ ውስጥ ከበባ ስድስት አሜሪካውያን ተገድለዋል፣ ቤን ጽዮን ክሮማን፣ ጋቭሪል ሆልትስበርግ፣ ሳንዲፕ ጄስዋኒ፣ አላን ሼሪ፣ ሴት ልጁ ናኦሚ ሼር፣ እና አሪዬ ሌቪሽ ትቴልባዩም፡፡

ወሮታ ለፍትህ ፕሮግራም ለነዚህ ጥቃቶች ተጠያቂ የሆኑ ግለሰቦችን በተመለከተ መረጃ እስከ 5 ሚሊዮን ዶላር ወሮታ ያበረክታል፡፡ የዚህ የዘግናኝ ሴራ ቁልፍ አባላት አሁንም አልተያዙም፣ ይህ ምርመራ አሁንም እየተካሄደ ነው እና ቀጣይነት ያለው ነው፡፡ ይህ ሽልማት ለድርጊቱ ተጠያቂ ለሆነ ለማንኛውም ግለሰብ ይሰጣል፡፡

ዴቪድ ኮልማን ሄድሌይ እና ታሃውር ራና የ LeT የሽብር ጥቃቶች ድጋፍ ሰጪ በመሆናቸው በአሜሪካ የፌዴራል ፍ / ቤት ተከሰዋል፡፡ እ.ኤ.አ በጥር 2013 ውስጥ በካፊል የፓኪስታን ዝርያ የሆነ የአሜሪካ ዜግነት ያለው ሲሆን፣ በ2013 በሙምባይ፣ ሕንድ ውስጥ በህዳር 2008 በተካሄዱ የሽብር ጥቃቶች ዕቅድ በማውጣት ረገድ የተጫወተውን ሚና በተመለከተና፣ እና ቀጥሎ በዴንማርክ አንድ ጋዜጣ ላይ ጥቃት ለመፈጻም በማቀዱ ከአስራ ሁለት የፌዴራል የሽብር ወንጀሎች ጋር በተያያዘ የ35 ዓመት እስራት ተፈርዶበታል፡፡ በመጋቢት 2010 ላይ በስድስት የአሜሪካዊያን ሰለባዎች የፈጸሙትን ግድያ ማበረታታትና መደገፍ ጨምሮ በርሱ ላይ በቀረቡት በ12 ጥፋቶች ላይ በደለኛ መሆኑን አምኖአል፡፡ ሄድሌ በሕንድ የህዝብ ቦታዎች ላይ የቦምብ ጥቃቶችን ለመፈጸም በማሴሩ ተፈርዶበታል፤ በሕንድ ውስጥ ህዝብን ለማጥቃት እና የአካል ጉዳት ለማድረስ በማሴሩ፣ በሕንድ የአሜሪካ ዜጎችን ለመግደል በማሴሩና በመደገፉ በሁሉም በስድስቱ ክሶች፣ በሕንድ ውስጥ ለሽብርተኝነት ቁሳዊ ድጋፍ ለመስጠት ማሴር፣ በዴንማርክ ውስጥ ሰዎችን ለመግደል እና ለማጥቃት በማሴር፣ በዴንማርክ ውስጥ ለሽብርተኝነት ቁሳዊ ድጋፍ ለመስጠት በማሴር፣ እና ለ LeT የቁሳቁስ ድጋፍ ለመስጠት በማሴሩ፡፡ የካናዳ ዜጋ የሆነችና የሄድሌይ የረዥም ጊዜ ጓደኛው ራና በዴንማርክ ለሽብርተኝነት ሴራ የቁሳቁስ ድጋፍ ለማቅረብ በማመቻቸት እና ለLeT ቁሳቁስ ድጋፍ በማቅረቧ የ14 ዓመት እስራት ተፈርዶባታል፡፡ እ.ኤ.አ. በሰኔ 2011፣ ራና በህዳር 2008 በሙምባይ ላይ ለተፈጸሙት የሽብር ጥቃቶች ከጥፋቱ የወንጀል ክስ ነጻ ሆናለች ነገር ግን በዴንማርክ ለሽብርተኝነት ሴራ የቁሳቁስ ድጋፍ ለማቅረብ በማመቻቸት እና ለLeT የቁሳቁስ ድጋፍ ለማቅረብ በመሳተፏ ተፈርዶባታል፡፡

የሚከተሉት ተጠርጣሪዎችም ደግሞ በአሜሪካ የፌዴራል ፍ / ቤት ተከስተዋል፡፡

  • ሳጂድ ሚር (Sajid Mir) – LeT የሽብር ጥቃቶችን ከማቀድ፣ ከመዘጋጀት፣ እና ከማከናወን ጋር በተያያዘ ድርጊቶቹን እንዲፈጽሙ ለታዘዙ ለዳዊት ሄድሌይና ለሌሎች እንደተቆጣጣሪሆኖ አገልግሏል፡፡
  • ማጆር ኢቅባል (Major Iqbal) – LeT በተፈጸሙት ጥቃቶች እቅድ ላይ ተሳታፊና በገንዘብ ዕርዳታ የተባበረ የፓኪስታን ኗሪ ነው፡፡
  • አቡ ካሃፋ (Abu Qahafa) – ለአሸባሪ ጥቃቶች ለማዋል ሌሎችን በውጊያ ስልቶች ያሰለጠነ LeT ጋር የተያያዘ የፓኪስታን ነዋሪ ነው ፡፡
  • ማህዛር እቅባል ፣ ደግሞ አቡ አል-ተብሎ የሚጠራው – የፓኪስታን ነዋሪ እና ከ LeT መሪዎች መካከል አንዱ ነው

የተጨማሪ ፎቶ

Mumbai Attacks - English PDF
Mumbai Attacks - Baluchi PDF
Mumbai Attacks - Hindi PDF
Mumbai Attacks - Pashto PDF
Mumbai Attacks - Urdu PDF