የሚፈለጉ
ፍትህ የሚያመጣ መረጃ…

ሙሐመድ አሕመድ አል-ሙናዋር

እስከ $5 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚደርስ ወሮታ

ሙሐመድ አሕመድ አል-ሙናዋር የሚፈለገው በፓኪስታን ካራቺ በአወሮፕላን መንደርደሪያ ላይ ነሐሴ 30 ቀን 1978 ዓ.ም. (እንደ እ አ.አ. ሴፕቴምበር 5 1986) በበረራ ቁ 73 የፓን አም አውሮፕላን ጠለፋ ጋር በተያያዘ ነው፡፡ ከላይ የተጠቀሰው ግለሰብ በሚከተሉት ወንጀሎች ተከሷል፡፡

በዩናይትድ ስቴትስ ላይ ጥቃት ለማድረስ በማሴር ከአሜሪካ ውጪ የሚኖሩ አማሪካውያንን ለመግደል በማሴር፣ ከአሜሪካ ውጪ የሚኖሩ አሜሪካውያንን ለመግደል ሙከራ በማድረግ፣ ከአሜሪካ ውጪ የሚኖሩ አማሪካውያን ላይ ከፍ ያለ የአካል ጉዳት በማድረስ፣ በእገታ፣ ለአመጽ ተግባር የጦር መሣሪያ በመጠቀም፣ በአውሮፕላን ላይ አደጋ የሚያደርስ መሣሪያ በማስቀመጥ፣ በአውሮፕላን ውስጥ ያሉ ሰዎችን የሚጎዳ አመጸኛ ተግባር በመፈጸም፣ የአውሮፕላን ላይ ዘረፋ በማካሄድ፣አውሮፕላንን የሚጎዳ ክፉ ተግባር በመፈጸምና ይህንኑ መርዳትና ማበረታታት፡፡

ዋዱድ ሙሐመድ ሀፊዝ አል-ቱርኪ፣ጀማል ሰኢድ አብዱል ራሒም፣ሙሐመድ አብዱል ካሊል ሑሴን አል ራሃያል እና ሙሐመድ አሕመድ አል ሙናዋር በኮሎምቢያ ዲስትሪክት የቀረበባቸው ክስ በፓኪስታን ካራቺ በአወሮፕላን መንደርደሪያ ላይ ነሐሴ 30 1978 ዓ.ም. (እንደ እ አ.አ. ሴፕቴምበር 5፣1986) በበረራ ቁ 73 ፓን አም አውሮፕላን ጠለፋ ውስጥ በነበራቸው ድርሻ ሰበብ ነው፡፡ በአውሮፕላኑ ውስጥ 78 አሜሪካውያንን ጨምሮ 379 ተሣፋሪዎችንና የበረራው ክፍል ሠራተኖችን ለ16 ሰዓታት በቁጥጥራቸው ሥር ካደረጉ በኋላ ጠላፊዎቹ እገሌ ከእገሌ ሳይሉ በጅምላ ወደ ተሣፋሪዎች በመተኮስ 20 ሰዎች ሲገድሉ 100 የሚሆኑት ደግሞ ከባድ የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል፡፡ እነዚህ ግለሰቦች አቡ ኒዳል የተባለ ዓለም አቀፋዊ የአሸባሪዎች ድርጅት አባላት እንደ ሆኑ ይታመናል፡፡

የተጨማሪ ፎቶ

የ--- ፎቶ ሙሐመድ አሕመድ አል-ሙናዋር