የሚፈለጉ
ፍትህ የሚያመጣ መረጃ…

ሙሀመድ አል- ጃውላኒ (Muhammad al-Jawlani)

እስከ $10 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚደርስ ወሮታ

ደግሞ አቡ ሙሀመድ አል – ጎላኒ ተብሎ የሚታወቀው ሙሀመድ አል – ጃውላኒ፣ ደግሞ ሙሀመድ አል- ጁላኒ ተብሎ የሚታወቀው፣ የአልቀይዳ የሶሪያ ቅርንጫፍ የአል- ኑስራህ (the al-Nusrah Front (ANF)) ግምባር የአሸባሪ ድርጅት አንጋፋ መሪ ነው።

እ ኤ አ በሚያዚያ 2013፣ አል- ጃውላኒ ታማኝነቱን ለአልቃይዳና ለመሪው አይማን አል- ዛዋሪ ሰጠ። በሀምሌ 16፣ በእንቴርኔት ቪዲዮ አል- ጃውላኒ አልቃይዳንና አል- ዛዋሪን አመስግኖአል እና ANF ስሙን ወደ ጃብሃት ፋት አል ሻም (“የሌቫንት ግምባር አሸናፊነት”) እንደ ቀየረ ተናግሮአል።

በአል- ጃውላኒ አመራር፣ANF ዘወትር ሲቪሎችን በማነጣጠር በመላው ሶሪያ በርካታ የአሸባሪነት ጥቃቶችን አካሄዶአል። በሚያዚያ 2015፣ ANF በሶሪያ ፍተሻ ጣቢያ በግምት 300 የኩርድ ሲቪሎችን አግቶ በኋላ እንደለቀቃቸው ተነግሮአል። በሰኔ 2015፣ ANF በሶሪያ፣ በዱሬዝ መንደር በቃልብ ላውዜህ 20 ኗሪዎችን ገድዬአለሁ ብሎ ኃላፊነት ወስዶአል።

በጥር 2017፣ ANF ሃያት ታህሪር ዓልሸም (Hayat Tahrir al-Sham (HTS) ከሌሎች በርካታ ጠንካራ ተቃዋሚ ቡድኖች ጋር ተቀላቅሎአል። ANF በሶሪያ የአልቃይዳ ጥምር ሆኖ ቀርቶአል። አል- ጃውላኒ የHTS መሪ ሳይሆን፣ በHTS ማዕከል በሆነው የANF መሪ ሆኖ ቀርቶአል።

ANF በእምግሬሽንና የብሄርተኝነት ህግ የውጭ አሸባሪ ድርጅት እና በሥራ መመሪያ 13224 በልዩ ሁኔታ የተመደበ አለም አቀፍ አሸባሪ እንደሆነ ተፈርጆአል።

የአሜሪካ የዉጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በሥራ መመሪያ 13224 መሠረት አል- ጃውላኒን በልዩ ሁኔታ የተመደበ አለም አቀፍ አሸባሪ ድርጅት እንደሆነ ፈርጆታል። እርሱም ደግሞ በተመድ የጸጥታ ምክር ቤት የ ISIL (Da’esh) እና የአልቃይደ ማእቀብ ኮሚቴ ተመዝግቦአል።

የተጨማሪ ፎቶ

Muhammad al-Jawlani English Poster
ሙሀመድ አል- ጃውላኒ (Muhammad al-Jawlani)