የሽብርተኝነት ድርጊቶች
መረጃ በ ...

የማሪን ኮር ሠፈር የቦንብ ጥቃት

ሊባኖስ እንደ አ | አ ጥቅምት 23 1983

በጥቅምት 23፣1983 በሊባኖስ ውስጥ በነበሩ የበርካታ አገሮች ሃይሎች አባላት በሆኑበት የአሜሪካና የፈረንሳይ ጥምር ሃይሎች መኖሪያ ላይ በመኪና ላይ የተጠመደ ፈንጅ ፈንድቷል፡፡ በጥቃቱም 241 የአሜሪካ ባህር ሃይል ወታደሮችን ጨምሮ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተገድለዋል፡፡ ጥምሩ ሃይል በሀገሪቱ የተሰማራ ሰላም አስከባሪ ነበር፡፡ ሂዝቦላ ይህንን ጥቃት ከኢራን ድጋፍና ገንዘብ አግኝቶ ፈጽሞታል ተብሎ ይታመናል፡፡

ወሮታ ለፍትህ ፕሮግራም ለነዚህ ጥቃቶች ተጠያቂ የሆኑ ሰዎችን ወደ ፍትህ ለማቅረብ የሚያስችሉ መረጃዎችን ለሚሰጡ ሰዎች እስከ 5 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚደርስ ወሮታ ያበረክታል፡፡ .