የሚፈለጉ
ፍትህ የሚያመጣ መረጃ…

መሊክ አቡ አብዴልካሪም

እስከ $3 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚደርስ ወሮታ

መሊክ አቡ አብዴልካሪም በእስላማዊ ማግሬብ ምድሮች (AQIM) በሚገኝ አልቀይዳ ተዋጊ ቡድኖች አንጋፋ መሪ ነው። በአብዴልካሪም አመራር፣ ድርጅቱ የጦር መሳሪያዎችን አግኝቶአል እና በሰሜንና በምዕራብ አፍሪቃ ውስጥ አፈናና ትንሽ የሽብርተኝነት ጥቃት አካሄዶአል። አብዱል ካሪም፣በሀምሌ 2010 የሰባ ስምንት ዓመት የፈረንሳዊ ምርኮኛን መግደሉ ተነግሮአል። በሰኔ 2010 በአብዴልካሪም ድርጅት በተፈጸመው ጥቃት 11 የአልጄሪያ ወታደሮችን ሞተዋል።

ቀድሞ የሰለፍስት ቡድን ለስብከትና ለውጊያ (GSPC) ተብሎ ይጠራ የነበረው በእስላማዊ ማግሬብ ምድሮች (AQIM) የሚገኝ አልቀይዳ በሰሜን አፍሪቃ አካባቢ በርካታ የሽብርተኝነት ጥቃት አካሄዶአል። AQIM ለአጥፍቶ ማጥፋት የቦምብ ጥቃት፣ምዕራባዊያንን አፈና፣ለግድያ፣ እቤት ውስጥ የተሰሩ የፈንጂ ጥቃቶችን ለማካሄዱ ኃላፊነቱን ወስዶአል። ቡድኑ በታህሳስ 2007 በተመድ ዋና ጽ/ቤትና በአልጄሪያ የህገ መንግሥት ምክር ቤት ባካሄደው ጥምድ የአጥፍቶ ማጥፋት የቦምብ ጥቃት 42 ሰዎች ሲሞቱ ሌሎች 158 ቆስለዋል። AQIM ደግሞ የሚሲዮናዊ ሥራ እያካሄደ እያለ በሰኔ 2009 ለተገደለው ለአሜሪካዊ ዜጋ ለክርስቶፌር ሌጌት ሞት ኃላፊነቱን ወስዶአል ። በመስከረም 2012፣ አባላቱ የአሜሪካንን ኤምባሲዎች እንዲያስፈራሩና አምባሰደሮችዋንም እንዲገድሉ አደፋፍሮአል። AQIM ከአልቀ ይዳ ጋር ስላለው ህጋዊ አንድነት በተመለከተ በመስከረም 2006 አስታውቆአል፣ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ የምዕራባዊያን ኢላማዎችን ለማጥቃት ያለውን ፍላጎት እንደገና አረጋግጦአል።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር በእምግሬሽንና የዜግነት አዋጅ ክፍል 219 መሰረት (በተሻሻለው)በመጋቢት 27፣2002 GSPCን አሸባሪ ድርጅት እንደሆነ ፈርጆታል፣እናም በጥቅምት 16፣2009 በአዲስ ስሙ AQIM ፍርጃውን አሳድሶአል። የአሜሪካ የገንዘብ ሚንስቴር ቡድኑን በየካቲት 21፣2008 በሥራ አፈጻጻም ትዕዛዝ 13224 ቡድኑን በልዩ ሁኔታ የተመደበ አሸባሪ እንደሆነ ፈርጆታል።