የሚፈለጉ
ፍትህ የሚያመጣ መረጃ…

ማሊም ሰልማን (Maalim Salman)

እስከ $3 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚደርስ ወሮታ

ማሊም ሰልማን አሁን በሞተው በአል- ሸባብ መሪ አህመድ አብዲ አው – መሀመድ ( ጎዳኔ)ለአል-ሸባብ የአፍሪካ የውጭ አገር ተዋጊዎች መሪ እንዲሆን ተመርጦአል። እርሱ ለአል-ሸባብ ሶማሊያዊ ያልሆኑ ተዋጊዎችን አሰልጥኖአል እና ጎብኚዎችን ፣ የመዝናኛ ሥፍራዎችን፣ እና ቤተ ክርስቲያናትን በማነጣጠር በአፍሪካ በውጊያ ተሳትፎአል።

ውጊያውን በዋናኛው ከሶማሊያ ውጭ ቢያተኩርም ቅሉ ፣ ሰልማን በሶማሊያ እንደሚኖርና የውጭ ተዋጊዎችን ወደ ሌላ ጋ ከመላኩ በፊት በሶማሊያዊ ውስጥ እንደሚያሰለጥን ታውቆአል። ከሽብርተኝነት ጥቃቶች መካከል ፣ አል-ሸባብ በኬንያ ፣ ናይሮቢ በዌስትጌት የገበያ አዳራሽ ተካሄዶ 65 ሰዎችን ለገደለው ለመስከረም 2013 ጥቃት ተጠያቂ ነበረ።