የሽብርተኝነት ድርጊቶች
መረጃ በ ...

የደብዳቤ ቦምብ አደጋዎች

እ.አ.አ ታህሳስ 1996 እስከ ጥር 1997


ከታህሳስ 1996 እስከ ጥር 1997 16 የደብዳቤ ቦምቦች የገና ስጦታ ካርዶች በማስመሰል በፖስታ ወደ አሜሪካና ወደ እንግሊዝ ተልከዋል፡፡.

ከነዚህ የደብዳቤ ቦምቦች ውስጥ አስራ ሦስቱ በኒው ዮርክ፣ በዋሽንግተን ዲሲ እና በለንደን በሚገኙት አል ሃያት ጋዜጣ ጽ/ቤቶች ተረክበዋል፡፡ በለንደን አንድ ቦምብ የፈንዳ ሲሆን ሁለት ንፁኃን ዜጎች በፁኑ ቆስለዋል፡፡ የቀሩት ሶስት ቦምቦች ዩናይትድ እስቴስ ውስጥ በሌቨንዋርዝ ባለው የፌደራል ወ ህነ ቤት ሊገኙ ችለዋል፡፡.

እያንዳንዱ ደብዳቤ አሌክሳንድሪያ ግብጽ መስከረም 21 ቀን 1996 የሚል የተጻፈበት ሲሆን የመልስ አድራሻ ግን አልተጻፈበትም:: የደብዳቤ ቦምቦቹ በነጭ ኢንቨሎቭ (ፖስታ) የታሸጉ ሲሆን በኮምፒዮተር የተጻፈ አድራሻ እና ሌሎች የተለያዩ ምልክቶችን የያዙ ናቸው፡፡.

ወሮታ ለፍትህ ፕሮግራም ለነዚህ ጥቃቶች ተጠያቂ የሆኑ ሰዎችን ወደ ፍትህ ለማቅረብ የሚያስችሉ መረጃዎችን ለሚሰጡ ሰዎች እስከ 5 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚደርስ ወሮታ ያበረክታል፡፡ .

የ-----ተጨማሪ ፎቶ

የደብዳቤ ቦምብ አደጋዎች