የሽብርተኝነት ድርጊቶች
መረጃ በ ...

የጠለፋና የግድያ ወንጀሎች

ለአሰርት አመታት ሊባኖስ ውስጥ በዘለቀው የእገታ ምስቅልቅል ከሂዝቦላ ጋር የሚገናኙ አሸባሪዎች የተለያዩ እገታዎችንና ግድያዎችን ፈጽመዋል፡፡ የእገታ ድራማው ከ1982 እስከ 1992 ዘልቋል፡፡

መጋቢት 16፣1984 አሸባሪዎች ቤይሩት ውስጥ የሲ አይ ኤ ሃላፊ የነበረውን ዊሊያም በክለይን በመጥለፍ ድብደባ በመፈፀም እስከ ተገደለበት ጊዜ ድረስ በግምት ለ15 ወራት በታጋችነት አቆይተውታል፡፡

ታህሳስ 3፣1984 የቤይሩት አሜሪካ ዩኒቨርስቲ ቤተ መጻህፍት ሠራተኛ የነበረው ፒተር ኪልቦርን ለመሰወሩ ሪፖርት ተደርጓል፡፡ ከ16 ወራት በኋላ እሱና ሌሎች ሁለት ታጋቾች ተገድለው ሬሶ ቻቸው በምስራቅ ቤይሩት ተራራ ላይ ተጥለው ተገኝተዋ ል፡፡

የካቲት 17፣1988 አሸባሪዎች ኮሎኔል ዊሊያም ሂጊንስን ከተባበሩት መንግሥታት የሠላም ማስከበሪያ መኪናው ጠልፈዋል፡፡ ኮሎኔሉ በምርኮ ወቅት ከመገደሉ በፊት ምርመራና ድብደባ ተደርጐበታል፡፡ የሞተበት ትክክለኛው ቀን አይታወቅም፡፡

ወሮታ ለፍትህ ፕሮግራም ለነዚህ ጥቃቶች ተጠያቂ የሆኑ ሰዎችን ወደ ፍትህ ለማቅረብ የሚያስችሉ መረጃዎችን ለሚሰጡ ሰዎች እስከ 5 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚደርስ ወሮታ ያበረክታል፡፡ .

ሰለባዎች

የ--- ፎቶ ዊሊያም ሂግንስ በ1989 ተገድሎአል
ዊሊያም ሂግንስ በ1989 ተገድሎአል
የ--- ፎቶ ፒቴር ክልብራም በ1986 ተገድሎአል
ፒቴር ክልብራም በ1986 ተገድሎአል
የ--- ፎቶ ዊሊያም ባክሌይ በ1985 ተገድሎአል
ዊሊያም ባክሌይ በ1985 ተገድሎአል