የሽብርተኝነት ድርጊቶች
መረጃ በ ...

በከሆባር ሕንጻዎች ላይ የተፈፀሙ የቦምብ ጥቃቶች

ደሃራን፣ ሳውዲ አረቢያ | ሰኔ 25፣1996

በሰኔ 25 ቀን 1996 በሳኡዲ አረብያ ዳህራን አቅራብያ በሚገኘው በኮባር ሕንጻዎች ላይ የሳኡዲ ሂዝቦላህ አባላት የአሸባሪ ጥቃት ፈጽመዋል፡፡ በዛ ወቅት ይህ ሕንጻ ለአሜሪካ ወታደሮች በመኖሪያነት ያገለግል ነበር፡፡ በዚህ ሕንጻ ላይ በቦነ ተሽከርካሪ ውስጥ በነበረ ልቁጥ ፈንጂ ፍንዳታ በተፈፀመ ጥቃት 19 የአሜሪካ ዜጎችና አንድ የሳኡዲ ዜጋ ሲገደሉ የተለያየ ዜግነት ያላቸው ሌሎች 372 ሰዎች ቆስለዋል፡፡.

በሰኔ 21 ቀን 2001፣ በቫርጅንያ የአሌክሳንድሪያ የፌደራል ከፍተኛ የፍርድ ሸንጎ በአሥራ አራት አሸባሪዎች ላይ ክስ መስርቷል፡፡ በተለያዩ የወንጀል ክሶች አህመድ አል ሙግ አሲልን፣ አሊ ኤል ሁሬን፣ ኢብራሂም አል ያከብ፣ አብድልከሪም አል ናስርና እና ሌሎች በርካታ ክስ ቀርቦባቸዋል፡፡ በዚህ ክስ መሰረትም ከአስራ አራቱ ዘጠኝ አሸባሪዎች በአርባ ስድስት የተለያዩ የወንጀል ድርጊቶች የተከሰሱ ሲሆን ለምሳሌም ያህል አሜሪካውያን እና የአሜሪካ መንግስት ሰራተኞችን ለመግደል በማሴር ወንጀል ብዙ ጥፋት የሚያደርሱ መሳሪያዎችን በመጠቀም ወንጀል እና የአሜሪካንን ሃብት የማውደም የማፈንዳት እና የግድያ ወንጀሎች ይገኙበታል፡፡.

ወሮታ ለፍትህ ፕሮግራም ለዚህ ጥቃት ተጠያቂ የሆኑ ሰዎችን ወደ ፍትህ ለማቅረብ የሚያስችሉ መረጃዎችን ለሚሠጡ ሰዎች እስከ 1 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚደርስ ወሮታ ያበረክታል፡፡.