የሽብርተኝነት ድርጊቶች
መረጃ በ ...

በአሜሪካ ኢምባሲዎች ላይ የተፈጸሙ የቦምብ ፍንዳታ ጥቃቶች

ኬንያ እና ታንዛኒያ እ.አ.አ | ነሀሴ 7፣ 1998

በነሀሴ 7 ቀን 1998፣ የአልቃይዳ አሸባሪ ቡድኖች አባላት ባንድ ጊዜ በደሬሳለም፣ ታንዛኒያ እና በናይሮቢ፣ ኬንያ፣ በአሜሪካ ኤምባሲዎች ላይ የቦምብ ጥቃቶችን አድርሰዋል፡፡ የወሮታ ለፍትህ መርሃ ግብር ለነዚህ ጥቃቶች ተጠያቂ የሆነውን ማንኛውም ግለሰብ ለፍትህ ለሚያቀርበው መረጃ እስከ $5 ሚሊዮን የሚደርስ ሽልማት ይሰጣል፡፡

በናይሮቢ፣ ፈንጂዎች የተጫኑባቸውን የጭነት መኪና የሚነዱ አሸባሪዎች በአሜሪካ ኤምባሲ የመኪና ማቆሚያ አጠገብ መኣት ቦምብ አፈንድተው ፣ 44 የኤምባሲ ሰራተኞችን (12 አሜሪካውያንና 32 የውጭ አገር ዜጎችን ) ጭምር 213 ግለሰቦችን ገድለዋል፣ እና የአሜሪካ አምባሳደር ፕሩዴንስ ቡሽኔልን ጭምር ከ5,000 በላይ ሌሎችን አቁስለዋል፡፡

በደሬሰላም፣ ፈንጂዎች የተጫኑባቸውን የጭነት መኪና የሚነዱ አሸባሪዎች የኤምባሲውን በር ለመግጨት ሞከሩ ፣ በኤምባሲው ላይ መተኮስ ጀመሩ፣ እና ከዚያም ፈንጂአቸውን አፈነዱ፡፡ ፍንዳታው 11 ሰዎችን ገድሎ 85 አቁስሎአል፡፡

የቦምብ ፍንዳታዎቹ በኤምባሲው ህንጻዎች ላይ ከባድ ጉዳት አስከትለዋል እና በቅርቡ የሚገኙትን ቢሮዎችንና ድርጅቶች አጥፍቶአል፡፡

ከጥቃቶቹ ጋር በተያያዘ የሚከተሉት ግለሰቦች ክስ ተመስርቶባቸው በአሜሪካ የፌዴራል ፍርድ ቤት ተፈርዶባቸዋል፤
  • ማምዱ ማህሙድ ሳሊም፣ የአልቃይዳ መስራች አባል፣ በ1998 በጀርመን ታይዞ ወጥቶአል፡፡ እርሱም ከጥቃቶቹ ጋር በተያያዘ ፍርድ ተፈርዶበት በፌዴራል ማራሚያ ቤት ለዕድሜ ልክ ታስሮአል፡፡   
  • በጥቅምት 2001፣ የአልቃይዳ ተዋጊዎች ዋዲህ ኤል – ሄግ ፣ ካልፋን ካሚስ መሀመድ፣ መሀመድ ራሺድ ዳውድ አል – ኦዋሊ፣ እና መሀመድ ሳዲክ ኦዴ የቦምብ ጥቃቶቹን ለማቀዳቸውና ለመፈጸማቸው የዕድሜ ልክ እስረት ተፈርዶባቸዋል፡፡
  • በጥር 2011፣ የአልቃይዳ ተዋጊ አህመድ ካሊፈን ጋይላኒ በቦምብ ጥቃቶች በነበረው ሚና በአሜሪካ ፍርድ ቤት የዕድሜ ልክ እስረት ተፈርዶበታል፡፡
  • በመስከረም 2014፣ የአልቃይዳ መሪ ዛዋህሪ የቅርብ ወዳጅ የነበረው አዴል አብዴል ባሪ፣ የአሜሪካ ዜጎችን ለመግደል በማሴሩ በፌዴራል ፍርድ ቤት የ25 አመት እሰራት ፍርድ ተፈርዶበታል፡፡  
  • በግንቦት 2015፣ ለኡሳማ ቢን ላዴን የምክትል የነበረው ካሊድ አል- ፋዋዝ፣ በቦምብ ጥቃቶች ጋር በተያያዘ የፌዴራል ፍርድ ቤት የዕድሜ ልክ እስረት ተፈርዶበታል፡፡
የሚከተሉት ቁልፍ ተጠርጣሪዎች ለቦምብ ጥቃቶቹ በፌዴራል ግራንድ ጁሪ ተፈርዶባቸዋል፤  

አይማን አል – ዛዋህሪ፣ የአሁኑ የአልቃይዳ መሪ  

ሳይፍ አል – አድል፣ የአልቃይዳ ቁልፍ መሪ

አብዱላሂ አህመድ አብዱላሂ፣ የአልቃይዳ ቁልፍ መሪ

ኡሳማ ቢን ላዴን፣ የቀድሞ የአልቃይዳ መሪ (ሞቶአል)

መሀመድ አቴፍ ፣ የአልቃይዳ ወታደራዊ መሪ (ሞቶአል)

አናስ አል – ሊቢ፣ የቀድሞ የአልቃይዳ መሪ (ሞቶአል)

የወሮታ ለፍትህ መርሃ ግብር ሳይፍ አል – አድል፣ እና አብዱላሂ አህመድ አብዱላሂ፣ የሚገኙበትን ቦታ ለመጠቆም፣ ለመያዝ ወይም ለፍርድ ለማቅረብ ወደሚያስችል መረጃ ለሚመራ ለያንዳንዱ ፣ እስከ $10 ሚሊዮን፣ እና በአይማን አል – ዛዋህሪ እስከ $25 ሚሊዮን የሚደርስ ሽልማት ይሰጣል፡፡  
በአሜሪካ ኤምባሲዎች ላይ ከደረሱት የቦምብ ጥቃቶች ጋር የተያያዙ የሽልማት ስጦታዎች

በአይማን አል – ዛዋህሪ

አብዱላሂ አህመድ አብዱላሂ

ሳይፍ አል – አድል፣

የተጨማሪ ፎቶ

English PDF
የ--- ፎቶ በአሜሪካ ኢምባሲዎች ላይ የተፈጸሙ የቦምብ ፍንዳታ ጥቃቶች
የ--- ፎቶ በአሜሪካ ኢምባሲዎች ላይ የተፈጸሙ የቦምብ ፍንዳታ ጥቃቶች
የ--- ፎቶ በአሜሪካ ኢምባሲዎች ላይ የተፈጸሙ የቦምብ ፍንዳታ ጥቃቶች
የ--- ፎቶ በአሜሪካ ኢምባሲዎች ላይ የተፈጸሙ የቦምብ ፍንዳታ ጥቃቶች