የሚፈለጉ
ፍትህ የሚያመጣ መረጃ…

ጅሃድ ሰርዋን ሞስጠፋ

እስከ $5 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚደርስ ወሮታ

ጄሃድ ሴርዋን ሞስጠፋ፣ደግሞ አህመድ ጉሬይ፣አንዋር አል- ምሪኪ፣ ኢምር፣አንዋር ተብሎ የሚታወቀው የአሜሪካ ዜጋና የድሮ የካልፎርኒያ ኗሪ ነው። እርሱም የሥልጠና ካምፕ መምህርና የውጭ ተዋጊዎች መሪ ሆኖ ጭምር ለአልሸባብ የተለያዩ ሥራዎችን ሠርቶአል። እርሱ ደግሞ በቡድኑ በሚድያ ድርጊቶች የሰለጠነ ነው። ሞስጠፋ በ2005 ዓ ም ወደ ሶማሊያ ከመሄዱ በፊት፣በሰንዲያጎ ካልፎርኒያ ይኖር የነበረ የአሜሪካ ዜጋ ነው።ሞስጠፋ የሚከተሉትን አካባቢዎችን ጎብኝቶ ይሆናል ወይም ሊጎብኝ ይችላል፤ ሶማሊያ፣የመን፣ኢትዮጵያ፣ኬንያ፣ሌላ የአፍሪካ አገሮች።

ሞስጠፋ በኤፍ ቢ አይ በጣም ተፈላጊ የአሸባሪዎች ዝርዝር ውስጥ አለበት፣እና በFBI በሽብርተኝነት ድርጊቶች ተጠርጥሮ ይፈለጋል። በጥቅምት 9, 2009፣በአሜሪካ የድስትርክት ፍ/ቤት፣በደቡብ ካልፎርኒያ ድስትርክት የፌዴራል የመያዝ መጥሪያ ወጥቶለታል። ሞስጠፋ በሚከተሉት ወንጀሎች ተከሶአል፤ ለአሸባሪዎች የማቴሪያል ድጋፍ በመስጠት ሴራ፣ለውጭ አሸባሪ ድርጅቶች የማቴሪያል ድጋፍ በመስጠት ሴራ፣እና ለውጭ አሸባሪ ድርጅቶች የማቴሪያል ድጋፍ በመስጠቱ ምክንያት ተከሶአል።

አልሸባብ በ2006 አጋማሽ ደቡብ ሶማሊያ የተቆጣጠረው የሶማሊያ እስላማዊ ፍ/ቤቶች የወታደራዊ ክንፍ ነበረ። አልሸባብ አመጸኛ ተግባሩን በደቡብና በማዕከላዊ ሶማሊያ ቀጥሎበታል። ቡድኑ፣ በዋናኛው የሶማሊያ ማዕከላዊ መንግስትንና የሶማሊያ ፌዴራሉን የሽግግር መንግሥት የሚደግፉትን ኢላማ በማድረግ በደቡብና በማዕከላዊ ሶማሊያ የተለያዩ የአጥፍቶ ጠፊ ቦምብ ጥቃቶች ጨምሮ በርካታ የቦምብ ድብደባ እንደካሄደ ኃላፊነቱ ወስዶአል። አልሸባብ በ2008 በሰሜን ሶማሊያ በሁለት ከተማዎች ኢላማዎች አድርጎ ቢያንስ 26 ሰዎችን ገድሎ ሌሎች 29 ሰዎችን ላቆሰሉ በአንድ ጊዜ ለአምስት ለተቀነባበሩ የአጥፍቶ ጠፊ የቦምብ ጥቃቶች ተጠያቂ ሊሆን ይችላል። አልሸባብ በሀምሌ 11፣2010 በካምፓላ፣ኡጋንዳ አንድ አሜሪካዊን ጨምሮ ከ70 ሰዎች በላይ ለገደለው ለመንታ የአጥፍቶ ጠፊ የቦምብ ፍንዳታ ተጠያቂ ነበረ። ቡድኑ የሶማሊያ የሰላም አቀንቃኞችን፣ዓለም አቀፍ የዕርዳታ ሠራተኞችን፣በርካታ የሲቭል ማህበረሰብ ተዋቂ ሰዎችንና ጋዜጠኞችን ለመግደሉ ተጠያቂ ነው። በየካቲት 2012፣አልሸባብና አልቀይዳ መደበኛ ትብብራቸውን ይፋ አድርገዋል።

የአሜሪካ የገንዘብ ሚንስቴር፣በክፍል 219 በእምግሬሽንና የዜግነት ህግ በየካቲት 26፣2008 (እንደተስተካከለው) በሥራ መመሪያ ትዕዛዘ (Executive Order) 13224. መሠረት በየካቲት 29፣2008 አል ሸባብን በተለየ ሁኔታ ዓለም አቀፍ አሸባሪ ድርጅትእንደ ሆነ ፈርጆታል።

የተጨማሪ ፎቶ

ጅሃድ ሰርዋን ሞስጠፋ
ጅሃድ ሰርዋን ሞስጠፋ