የሽብርተኝነት ድርጊቶች
መረጃ በ ...

የISIS የአፈና መረቦች

የአሜሪካ የወጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ወሮታ ለፍትህ መርሓ ግብር የISIS የአፈና መረቦችን ወይም ለክርስቲያን ቄስ ማሄር ማህፉዝ፣ ሚካኤል ካያል፣ ግሪጎሪኦስ ኢብራሂም፣ ቦሎኡስ ያዚጊ፣ እና ፓኦሎ ዳሎግሊኦ አፈና ሓላፊነት ወዳለባቸውን ሰዎች ጋ ለሚያደርስ መረጃ እስከ $5 ሚሊዮን የሚደርስ ወሮታ ይሰጣል፡፡ እነዚህ ወሮታዎች እየተሰጡ ያሉት ከISIS ጋር በምንዋጋበት አስፈላጊ በሆነ ወቅት ነው፡፡ የሃይማኖት መሪዎች አፈና የሚያሳየው የ ISIS ጫካኝ ስልቶችንና የዋህ ግለሰቦችን የማነጣጠር እሽታን ነው፡፡

እ ኤ አ በየካቲት 9 ቀን 2013፣ የግሪክ ኦርቶዶክስ ቄስ ማሄር ማህፉዝ እና የአርማኒያ የካቶሊክ ቄስ ሚካኤል ካያል በህዝብ አውቶቡስ በካርፉን፣ ሶርያ ወደሚገኛው ገዳም እየሄዱ ነበረ፡፡ በግምት ከአሌፖ 30 ኪ ሜ ውጭ፣ ተጠርጣሪ የ ISIS አክራሪዎች መኪናውን አቁመው፣ የተጓዦችን ሰነዶችን ፈትሸው ሁለቱን ቄሶች ከአውቶቡስ አወጡአቸው፡፡ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ እነርሱ አልታዩም ወይም ማንም ስለነርሱ አልሰማም፡፡

በሚያዚያ 22 ቀን 2013 የሶሪያ ኦርቶዶክስ ሊቃነ ጳጳሳት ግሪጎሪኦስ ኢብራሂም፣ የግሪክ ኦርቶዶክስ ቄስ ቦሎኡስ ያዚጊን ለመውሰድ ከአሌፖ፣ ሶሪያ ወደ ቱርክ ሄዱ፡፡ እነርሱም በአል መንሱራ፣ ሶሪያ አጠገብ ወደ ፍተሻ ጣቢያ ሲደርሱ፣ ብዙ መሳሪያ የታጠቁ ሰዎች አድፍጠው መኪናቸውን ማረኩ፡፡ የቄሱ ነጂ በኋላ ሞቶ ተገኝቶአል፡፡ ሊቃና ጳጳሳቱ ከጃብሃት አል ኑስራ ግምባርና ከአልቀይዳ ጋር ከተያያዙ ሰዎች ጋር እንደታፈኑ ይታመናል፣ ዳሩ ግን፣ ሊቃና ጳጳሳቱ በኋላ ወደ ዳኤሽ በመባል ወደሚታወቀው ISIS ተላልፈዋል፡፡

በሀምሌ 29 ቀን 2013፣ ISIS በራቃ የኢጣሊያ ጀሷዊ ቄስ ፓኦሎ ዳሎግሊዮን ጠልፎአል፡፡ አባት ዳሎግሊዮ ከባቶች ማህፉዝ እና ካያል፣ እና ሊቃና ጳጳስ እብራሂምና ያዚጊ መለቀቅ በተመለከተ ከ ISIS ጋር ለመገናኘት እቅድ ነበራቸው፡፡ እርሳቸውም ከዚያ ወዲያ አልታዩም ወይም ማንም ስለርሳቸው አልሰማም፡፡

ISIS ለአሜሪካ፣ እንዲሁም በመላው መካከለኛ ምስራቅና በአለም ዙሪያ ላሉት አባሮችዋና አጋሮችዋ ዋና አስጊ ሆኖአል፡፡ እኛ በእራቅና በሶሪያ ያሉ አጋሮቻችን ይህንን የአሻባሪ ስጋት ለማሸነፍ በሚያደርጉት ጥራቶቻቸው እንደግፋቸዋለን፣ እና በመለው አለም በየትም ቦታ ISIS መጠለያ እንዳያገኝ ከአለም አቀፍ ህብረት ጋር ትብብራችንን እናጠናክራለን፡፡ ISIS የተቋቋመው በ2004 በአክራሪ አቡ ሙሳብ አል ዘርካዊ እንደ “አልቁይዳ በኢራቅ” ወይም AQI ተብሎ ነበረ፡፡ ቡድኑ በኋላ “ የኢራቅ እስላማዊ መንግስት” ተብሎ ይታወቃል፡፡

ISIS አባላቱ ክፉ፣ የተቀናጀ የሰብአዊ መብቶችንና ሌሎች መጥፎ ነገሮች በካሄዱባቸው በኢራቅና በሶሪያ እንዲዋጉ ከመላው አለም በሺዎች የሚቆጠሩ ተከታዮችን መልምሎአል፡፡ የISIS አባላት በመላው ማህበረሰብና በግለሰቦች ላይ አነጣጥረው በጅምላ ጨፍጭፈዋል፣ ልጆችን ገድለዋል እና ቆራረጥዋል፣ አስገድደው ደፍረዋል፣ ሰውን ጠልፈዋል እና ሌላ አመጽ አካሄደዋል፡፡ ISIS በተቆጣጠረባቸው ማህበረሰብሎች ውስጥ የዚድሶችን፣ ክርስቲያኖችንን፣ የሺያ ሙስሊሞችን ገድሎአል፣ በሰው ላይ ወንጀል ፈጽሞአል፣ እና በነዚያ ቡድኖችና በሱኒ ሙስሊሞች፣ በኩርዶች፣ በሌላ አናሳ ቡድኖች ላይ የጎሳ ጠረጋ ወይም ጥፋት አካሄዶአል፡፡ በሚያዚያ 2013፣ የአሁኑ የ ISIS መሪ አቡ ባካር አል ባግዳዲ የኢራቅ እስላማዎ መንግስት በ ISIS ቁጥጥር ውስጥ እንደሚሰራ ለህዝብ ይፋ አድርጎአል፡፡ በሰኔ 2014፣ ዳኤሽ ተብሎ የሚታወቀው ISIS የሶሪያንና የኢራቅን የተወሰኑ ክፍሎችን ተቆጣጥሮ በራሱ የእስላማዊ ካልፌት ብሎ ሰይሞታል እና አል ባግዳዲን ካልፍ ብሎታል፡፡ በአሁኑ አመታት፣ ISIS የጂሃዳዊ ቡድኖችን ታማኝነት አትርፎአል፣ እና በአሜሪካ ላይ ጥቃት እንዲፈጽሙ በማነሳሳት አለም ላይ የግለሰቦችን አእምሮ ቀይሮአል፡፡

የተጨማሪ ፎቶ

ISIS Kidnapping Networks - English
ISIS Kidnapping Networks - French
ISIS Kidnapping Networks - Kurdish
ISIS Kidnapping Networks
Mahfouz
Kayyal
Gregorios
Yazigi
Paulo