የሽብርተኝነት ድርጊቶች
መረጃ በ ...

እስላማዊ አብዮታዊ ጥበቃ ቡድን

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ወሮታ ለፍትህ መርሃ ግብር IRGC-Quds Force (IRGC-QF) ን ጭምር የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ጥበቃ ቡድን (IRGC) ቅርንጫፎቹን የገንዘብ ምንጮችን ወደሚያደናቅፍ እርምጃ ለሚመራ መረጃ እሰክ $15 ሚሊዮን የሚደርስ ሽልማት ይሰጣል፡፡ IRGC በዓለም ዙሪያ ለበርካታ የሽብር ጥቃቶች እና ተግባሮች የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል ፡፡ IRGC-QF እንደ ሂዝባላና ሃማስ በመሳሰሉት ግብረ አባሮችዋ አማካይነት ከኢራን ውጭ የኢራን የሽብርተኝነት ተግባሮችን ይመራል ፡፡

ሚንስቴሩ የሚከተሉትን ጭምር የIRGC ፣ IRGC-QF ፣ የቅርንጫፎቹ የገቢ ምንጭ ወይም ቁልፍ የገንዘብ ማመቻቸ ስልቶች ላይ ለሚቀርብ መረጃ ሽልማት ይሰጣል፡፡

  • IRGC ህገወጥ የገንዘብ እቅዶች፣ ዘይት ለገንዘብ ጭምር ፣
  • ከIRGC ጋር የተሳሰሩ የፊት ኩባንያዎች፣ በእነርሱ ምትክ በዓለም አቀፍ ሥራ ተሰማርተዋል፣
  • የአሜሪካንና እና የዓለም አቀፍ ማዕቀቦችን በማምለጥ IRGCን የሚረዱ አካላት ወይም ግለሰቦች፣
  • ከ IRGC ጋር የንግድ ሥራ የሚሰሩ መደበኛ የፋይናንስ ተቋማት ፣
  • IRGC እንዴት ገንዘብ እና ቁሳቁሶችን ለአሸባሪዎቹ እና ለወታደራዊ ግብረ አባሮቹና አጋሮች እንደሚያስተላልፍ፣
  • የIRGC ለጋሾች ወይም የገንዘብ አስተባባሪዎች ፤
  • የ IRGC ግብይቶችን የሚያመቻቹ የገንዘብ ተቋማት ወይም መለወጫ ቤቶች፤
  • በ IRGC ወይም በገንዘብ ተቆጣጣሪዎች የተያዙ ወይም ቁጥጥር የሚደረግባቸው ንግዶች ወይም ኢንቨስትመንቶች ፣
  • በIRGC ፈንታ፣ በዓለም አቀፍ የሁለትዮሽ አጠቃቀም ቴክኖሎጂ ግዥ የተሰማሩ የፊት ኩባንያዎች ፤ እና
  • ድርጅቱን በገንዘብ የሚጠቅሙ የ IRGC አባላትን እና ደጋፊዎችን የሚመለከቱ የወንጀል መርሃግብሮች ፡፡

IRG የኢራን አብዮት ከተጀመረ በኋላ እ.ኤ.አ. በ 1979 ተመሠረተ ፡፡ ይህ የኢራን ወታደራዊ ቅርንጫፍ ሲሆን በዋነኝነት በበኩድ ሃይሎች (Qud Force) አማካይነት፣ IRGC ተዋናዮች የአገዛዙን ዓለም አቀፍ የሽብር ዘመቻ በመምራትእና በማከናወን ረገድ ትልቁን ሚና አላቸው ፡፡

በሚያዚያ 15 ቀን 2019 የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር፣ IRGCን በኢሚግሬሽን እና በብሔረሰብ ሕግ ክፍል 219 መሠረት የውጭ አሸባሪ ድርጅት አድርጎ ወስኗል ፡፡ እ.ኤ.አ. በ 2017 የአሜሪካ የገንዘብ ሚንስቴር IRGCን ፣ በሥራ አፈፃፀም ትዕዛዝ 13224 መሠረት IRGCን IRGC-QF በመደገፍ ተግባሮቹ ምክንያት በልዩ ሁኔታ የተመደበ አለም አቀፍ አሸባሪ አድርጎ ፈርጆታል ፡፡

ከ40 ዓመታት በፊት ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ IRGC በአሸባሪነት ሴራ ውስጥ የተሳተፈ ሲሆን በዓለም ዙሪያ ሽብርተኝነትን ይደግፋል ፡፡ IRGC የአሜሪካ ዜጎችን የገደሉትን ጥቃቶች ጨምሮ የአሜሪካ እና በአሜሪካ ድርጅቶች ላይ ላነጣጠሩ ለበርካታ ጥቃቶች ተጠያቂ ነው፡፡ IRGC በአሜሪካ እና በተባበሪዎቹ ወታደሮች ላይ በኢራቅ እና በአፍጋኒስታን በሚገኙት የዲፕሎማቲክ ተልእኮዎች ላይ ጥቃቶችን ደግፎአል፡፡

በተጨማሪም፣ ቡድኑ ዛሬ ብዙዎቹ በእራን የሚገኙትን በርካታ ምርኮኞችን ጭምር አሜሪካዊያንን ማርኮአል እና በስህተት በቁጥጥር ስር አድርጎአቸዋል ፡፡

IRGC–QF እንደ ጀርመን ፣ ቦስኒያ ፣ ቡልጋሪያ ፣ ኬንያ ፣ ባህሬን ፣ ቱርክ እና አሜሪካ ባሉ አገሮች ላይ በዓለም ዙሪያ የሽብር እንቅስቃሴዎችን አቅዶአል ፡፡

የተጨማሪ ፎቶ

እስላማዊ አብዮታዊ ጥበቃ ቡድን
እስላማዊ አብዮታዊ ጥበቃ ቡድን
እስላማዊ አብዮታዊ ጥበቃ ቡድን
እስላማዊ አብዮታዊ ጥበቃ ቡድን
እስላማዊ አብዮታዊ ጥበቃ ቡድን
እስላማዊ አብዮታዊ ጥበቃ ቡድን
እስላማዊ አብዮታዊ ጥበቃ ቡድን