የሚፈለጉ
ፍትህ የሚያመጣ መረጃ…

አብዴልቃድር መሀመድ አብድልቃድር

እስከ $3 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚደርስ ወሮታ

እክሪማ ተብሎ የሚታወቀው አብዴልቃድር መሀመድ አብድልቃድር እ ኤ አ በ1979 ዓ ም በኬንያ ተወለደ። እርሱም የአል-ሸባብ አስተባባሪና የድርጊት አቃጅ ነው።

አል-ሸባብ፣በ2006 አጋማሽ አብዛኛውን የደቡብ ሶማሊያን የተቆጣጠረው የእስላማዊ ፍርድ ቤቶች ምክር ቤት የወታደራዊ ክንፍ ነው። አል-ሸባብ ጠበኛ የሆነውን ጣልቃ ገብነት በደቡብና በማዕከላዊ ሶማሊያ ቀጥሎአል። ቡድኑ ለበርካታ የቦምብ ፍንዳታዎች ኃላፊነቱን ወስዶአል – በዋናኛው በሶማሊያ መንግሥት ባለሥልጣኖችንና በታወቁ የሶማሊያ ፌዴራላዊ የሽግግር መንግሥት ግብረ አባሮች ላይ በሞቃዲሾና በማዕከላዊና በሰሜናዊ ሶማሊያን ጨምሮ የተለያዩ ዓይነት የአጥፍቶ ጠፊ ጥቃቶችን ፈጽሞአል። አል-ሸባብ በከምፓላ፣ኡጋንዳ በሀምሌ 11፣2010 ፈንድቶ፣አንድ አሜሪካዊን ጨምሮ ፣ ከ70 በላይ ሰዎችን ለገደለው ለድርብ የአጥፎ ጠፊ የቦምብ ጥቃቶች ተጠያቂ ነበረ። ቡድኑ ደግሞ የሶማሊያ የሰላም አቀንቃኞችን፣ዓለም አቀፍ የዕርዳታ ሠራተኞችንና፣በርካታ የሲቪል ማህበራት ተዋቂ ሰዎችን፣እና ጋዜጠኞችን ገድሎአል።

የኣሜሪካ የዉጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በክፍል 219 የእምግሬሽንና የዜግነት አዋጅ (እንደ ተሻሻለው) በየካቲት 26፣2008፣እና በየካቲት 29፣2008 በሥራ አፈጻጸም ትዕዛዝ 13224 መሠረትአልሸባብን የውጭ አሸባሪ ድርጅት እንደሆነ ፈርጆታል። በየካቲት 2012፣አልሸባብና አልቀይዳ መደበኛ የሆነ ህብረታቸውን አሳውቀዋል።