የሚፈለጉ
ፍትህ የሚያመጣ መረጃ…

ኢብራሂም ሳልህ መሀመድ አል-ያቁብ

እስከ $5 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚደርስ ወሮታ

ሰኔ 25፣1996 ላይ የሳውዲ ሂዝቡላ አባላት ሳውዲ አረቢያ ውስጥ ዳህራን አጠገብ በሚገኘው የኩበር ስቀላ የመኖሪያ ቤት ክልል ወይም ግቢ ላይ የሽብር ጥቃት አደረሱ፡፡ አሸባሪዎቹ በልቁጥ ፈንጅዎችና ተቀጣጣዮች የተሞላን ቦቴ በመንዳት በመኪና ማቆሚያ ክልል ውስጥ አቁመውት በርቀት መቆጣጠሪያ መሳሪያውን እንዲፈነዳ አድርገዋል፡፡ ሁሉም በቅርብ ርቀት የነበሩ ህንፃዎች ወድመዋል:: በዚህ ጥቃት በአገልግሎት ላይ የነበሩ 19 ሰዎችና አንድ የሳውዲ ተወላጅ ተገድለው ከብዙ የተለያዩ ዜጎች የተገኙ ሌሎች 372 ደግሞ ቆስለዋል፡፡

ከላይ የተጠቀሰው ግለሰብ የቨርጅኒያ ምስራቃዊ ዲስትሪክት ፍርድ ቤት እ.አ.አ. ጁን 25/1996 ዳህራን ሳውዲ አረቢያ ውስጥ በኩበር ሰቀላ ወታደራዊ ቤት ክልል ላይ ለደረሠው የቦምብ ጥቃት ተጠያቂ አድርጎታል፡፡

ከላይ በሥም የተጠቀስው ግለሰብ በሚከተሉት ክሶች ተወንጅሏል:

የአሜሪካ ዜጎችንና ሰራተኞችን ለመግደል ማሴር በአሜሪካ ዜጎች ላይ ጅምላ ጨራሽ የጦር መሳሪያዎችን ለመጠቀም ማሴር የአሜሪካ ንብረቶችንና ወታደራዊ ተቋማትን ለማውደም ማሴር ሞትን ያስከተለ የቦምብ ጥቃት መፈፀም በአሜሪካ ዜጎች ላይ ጅምላ ጨራሽ የጦር መሳሪያዎችን መጠቀም የሀይል ተግባር ወንጀል በመፈፀም ሂደት አጥፊ መሳሪያን በመጠቀም የአሜሪካ ዜጎችን መግደል የፌደራል ተቀጣሪዎችን በግፍ መግደልና የፌደራል ተቀጣሪዎችን ለመግደል መሞከር

የ-----ተጨማሪ ፎቶ

ኢብራሂም ሳልህ መሀመድ አል-ያቁብ