የሚፈለጉ
ፍትህ የሚያመጣ መረጃ…

ሁሳይን ሙሐመድ አል ኡማሪ

እስከ $5 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚደርስ ወሮታ

ሁሴይን ሙሐመድ አል ኡማሪ በኤፍ ቢ አይ የሚፈለገው በነሐሴ 5 ቀን 1974 ዓ.ም. (እንደ አ.አ. ኦገስት 11 ቀን 1982) አንድ መንገደኛ በሞተበት፣16 መንገደኞች በቆሰሉበትና 267 መንገደኞችና የበረራው ሠራተኞች ሊገደሉ በተቃጣበት ፓን አሜሪካን ወርልድ ኤየርዌይስ በረራ ቁ 830 ላይ የቦምብ አደጋ ለማድረስ ሙከራ በመጠርጠሩ ነው፡፡ አል ኡማሪ በዚህ አሸባሪ ተግባር ከተከሰሱት ሦስት ሰዎች አንዱ ሲሆን አውሮፕላኑ ከጃፓን ናሪታ ወደ ሐዋይ ሆኖሉሉ ሲበር በውስጡ የፈነዳውን ቦምብ ያቀደውና ያዘጋጀው እርሱ እንደሆነ ይጠረጠራል፡፡

አል ኡማሪ በኮሎምቢያ ዲስተርክት በ አሜሪካ ዲስትርሪክቱ ፍርድ ቤት ክሱ የቀረበበት በ፤ (1) በንብረት ላይ ውድመትና ጥፋት ለማድረስ በማሴር፣ (2) ግድያ ለመፈጸም በማሴር፣ (3) በግድያ፣ (4) አውሮፕላን በማበላሸት፣ (5) በውጭ የንግድ በረራ ላይ ያለ አውሮፕላንን በማውደም፣ (6) በአውሮፕላን ላይ ቦምብ በማጥመድ፣ (7) ጥቃት በማድረስ፣ (8) አውሮፕላን ለማበላሸት በመሞከር፣(9) በመደገፍና በማበረታታት ነበር፡፡ በአውሮፕላኑ ላይ ቦምቡን ያጠመደው ግብረ አበሩ ሙሐመድ ራሺድ በ1990 ዓ.ም. (እንደ እ አ.አ. በ1998) በቁጥጥር ስር ውሎ ወደ አሜሪካ እንዲመጣ ተደርጓል፡፡ ቃል በገባው መንስኤ በቦምብ ጥቃቱ የነበረውን ሚናና ጥፋተኛነቱንም አምኖ ለመተባበር ስምምነት ፈርሟል፡፡

የቦምብ ሥራ ሊቅ እንደሆነ የሚታመነውና በአንድ ወቅት “15 ሜይ” የተባለ የአሸባሪዎች ቡድን አባል የነበረው አል ኡማሪ በ1977 ዓ.ም. (እንደ እ አ.አ. በ1985) በፓሪስ ከተማ ማርክስ እና ስፔንሰር የገበያ ቦታ እንዲሁም በሌኡሚ ባንክ የቦምብ ፍንዳታ ድርሻው በፈረንሳይ መንግሥት ክስ ቀርቦበታል፡፡

አል ኡማሪ ሚስቱ ትኖርበታለች ተብሎ ከሚነገረው ሊባኖስ ፓስፖርት ሊኖረው ይችላል፡፡ የሁለት ወንዶችና የሁለት ሴቶች ልጆች አባት ነው፡፡ በኢራቅ ለበርካታ ዓመታት ኖሯል፡፡ አሁን የት እዳለ ባይታወቅም ሊባኖስ ወይም ኢራቅ ሊኖር ይችላል፡፡ መሣሪያ ታጥቆ የሚዘዋወር መሆኑ ስለሚነገር አደገኛና የታጠቀ መሆኑ ሊታሰብ ይገባል፡፡

የ-----ተጨማሪ ፎቶ

ሁሳይን ሙሐመድ አል ኡማሪ