የሚፈለጉ
ፍትህ የሚያመጣ መረጃ…

ሀሰን ኢዛልዲን

እስከ $5 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚደርስ ወሮታ

ይህ አሸባሪ የሊባኖሱ አሸባሪ ድርጅት የሂዝቡላ አባል ነው ተብሎ ይታመናል፡፡

ሰኔ 14፣1985 ከአቴንስ፣ ግሪክ ወደ ሮም፣ ጣሊያን በማምረት ላይ የነበረው ቲደብሊው ኤ 847 አውሮፕላን አሸባሪዎች ጠለፉ፡፡ ወደ በርካታ ቦታዎች ከበረረ በኋላ አይሮፕላኑ ቤይሩት ሊባኖስ ውስጥ አረፈ፡፡ በዚያ ጠለፋ የአሜሪካ ኃይል ባህርተኛ የሆነውን ሮበርት ስቴትዛምን እዚያ ገድለውት የሟችን ሬሳ በአውሮፕላን ማረፊያ ሜዳው ላይ ጣሉት፡፡

ይህ አሸባሪም በሰኔ 14፣1985 የንግድ አውሮፕላን ጠለፋ በማቀድና በመሳተፍ ተግባር ተፈላጊ ነው፡፡ በዚህ የአውሮፕላን ጠለፋ ወቅት ብዙ ተጓዦችና የበረራው አባላት ላይ አካላዊ ጥቃት ተሰንዝሮ አንድ አሜሪካዊ ዜጋ ተገድሏል፡፡

ከላይ በሥም የተጠቀስው ግለሰብ በሚከተሉት ክሶች ተወንጅሏል:

የአውሮፕላን ውንብድና ለማድረግ ማሴር፣ አውሮፕላን መጥለፍ፣ ግድያን ያስከተለ የአውሮፕላን ውንብድና መፈፀም፡፡ በረራን ማስተጓጎል፣ በአውሮፕላን ላይ አውዳሚ መሳሪያ ማስቀመጥ፣ ፈንጂ አውሮፕላን ላይ ማጥመድ፣ በተጓዦችና የበረራ አባላት ላይ አካላዊ ጥቃት መፈፀም፣ ግድያን ያስከተለ የአውሮፕላን ውንብድና መፈፀም፣ አደገኛ መሳሪያዎችን በመጠቀም ጠለፋ ለመፈፀም መሞከር፣ በሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ማድርስ፣ ሽብርን መደገፍ፣ ማበረታታት፡፡