የሚፈለጉ
ፍትህ የሚያመጣ መረጃ…

ሀመድ ኤል ካህሪ

እስከ $5 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚደርስ ወሮታ

ሀመድ ኤል ካህሪ በምዕራብ አፍሪቃ አንድነትና ጅሃድ (MUJWA፣ደግሞ MUJAO እና TWJWA ተብሎ ለሚጠረው ) የተባለ የሽብርተኛ ቡድን እንቅስቃሴ መሪና መስራች አባል ነው።  በካህሪ አመራር፣ የMUJWA የአባላት አሸባሪዎች የአፈና ተግባሮችን፣ የሽብርተኝነትጥቃቶችን፣እና የውጭ ድፕሎማቶችን ጠለፋ አካሄደዋል።  ካህሪ እ ኤ አ ለሚያዚያ 2012፣በማሊ ሰባት የአልጄሪያ ድፕሎማቶችን ለማፈኑ ኃላፊነት ወስዶአል፣እና ድርጅቱን በሚቃወሙት ላይ በMUJWA ቪድዮ ውስጥ ዛቻውን ሰንዝሮአል።  በጥር፣ 2012፣ የMUJWA ግብ “በመለው ምዕራብ አፍሪቃ የሸሪያ ህግ ለመጫን” እንደሆነ ከህሪ ገልጾአል።

በMUJWA የአመራራ ሚና ሳይኖረው በፊት፣ካህሪ የAQIM አባል ሆኖ፣በማውርታኒያ ላይ የሽብርተኝነት ድርጊቶቶችን ያቅድ ነበረ።  በጥቅምት2011፣ካህሪ በአልጄሪያ ሁለቱን በጠብመንጃ ባቆሰለው የሦሥት የዕርዳታ ሠራተኞችን አፈና አዝዞአል።  ካህሪ በታህሳስ 7፣2012 በሥራ አመራር ትዕዛዝ 13224 መሠረት አሸባሪ እንደሆነ ተፈርጆበታል።

MUJWA በመለው የምዕራብ አፍሪቃ የሽብርተኝነትተግባሮችን ለማፋፋም በእስላማዊ ማግሬብ ከሚገኘው አልቀይዳ (AQIM) ተገንጥሎ በመስከረም 2011 ተመሰረተ።  MUJWA በመጋቢት 2012 በአልጄሪያ፣ተመንራሴት 23 ሰዎችን ያቆሰለውን ጨምሮ የተለያዩ ጥቃቶችንና አፈናዎችን አካሄዶአል።  MUJWA ደግሞ የከናዳ አምባሳደርንና የተመድ መልእክተኛ ሮቤርት ፎውሌርን ለማፈኑ ኃላፊነት ወስዶአል።   አሜሪካ MUJWAን በታህሳስ 7፣2012 ልዩ ዓለም አቀፍ አሸባሪ እንደሆነ ፈርጀዋለች፣እና በአልቃይዳ ላይ ማዕቀብ የሚጥለው የተመድ ኮሚቴ በታህሳስ 5፣2012፣ከAQIM ጋር የሚገናኝ መሆኑን በዝርዝር ውስጥ አስገብቶአል።