የሚፈለጉ
ፍትህ የሚያመጣ መረጃ…

የሚገኝበትን ቦታ ለሚያሳይ መረጃ

እስከ $2 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚደርስ ወሮታ

ሃፊዝ አብዱል ራማን ማኪ በፓኪስታንና በህንድ ክፍሎች ላይ የእስላማዊ ህግ ለመመስረት ቆርጦ ለተነሰው ለላሽካር ኢ ታይባ፣የአክራሪ አህል ኢ እስላማዊ ድርጅት ሁለተኛ አዛዥ ነው። ለላሽካር ኢ ታይባ በሙምባይ፣ስድስት የአሜሪካ ዜጎችን ጨምሮ 166 ሰዎችን የገደለውን የህደር 2008 የሽብርተኝነት ጥቃትና እንዲሁም በህንድ ሌሎች በርካታ የሽብርተኝነት ጥቃቶችን እንዳደረጀና እንዳካሄደ ይታመናል።

የአሜሪካ የገንዘብ ሚንስቴር በሥራ መመሪያ ትዕዛዘ (Executive Order) 13224.ማኪን በልዩ ሁኔታ የተፈረጀ ዜጋ እንደሆነ ፈርጆታል።

ላሽካር ኢ ታይባ በታህሳስ 2001 የውጭ አገር አሸባሪ ድርጅት እንደሆነ ተፈርጆበታል።በሚያዚያ፣2008 አሜሪካ ጀማት ኡድ ዳዋን የውጭ አገር አሸባሪ ድርጅትእንደሆነ ፈርጀበታለች። እንዲዚያውም፣በታህሳስ፣2008 የተባበሩት መንግሥታት ጀማት ኡድ ዳዋን አሸባሪ ድርጅት እንደሆነ ፈርጆበታል።