የሽብርተኝነት ድርጊቶች
መረጃ በ ...

የጆን ግራንቪልና አብዴልረሃማን አባስ ግድያ

ካርቱም፣ሱዳን | ጥር 1, 2008

በጥር 1, 2008፣ የዩስ ኤስ ዜጋና የአሜሪካ የዓለም አቀፍ ልማት ድርጅት(USAID) ሠራተኛ እና ሱዳናዊ ሾፌሩ አብዴልረሃማን አባስ ረህማን፣በካርቱም ሱዳን ከአዲስ ዓመት ዋዜማ በዓል ወደ ቤታቸው ሲመለሱ ተተኩሶባቸው ሞተዋል። ሁለት ቡድኖች ፣አንሳር አል- ታውሂድ (በአንድ አምላክ የሚያምኑትን ደጋፊዎች) እና በሁለት አባይ ወንዞች መካከል ባለው ምድር አልቃይዳ (AQTN) በተናጠል ለግድያው ኃላፊነቱን ወስደዋል።

የሱዳን ህግ አካል በግድያ በመሳተፋቸው በአምስት ሰዎች ላይ ክስ መስርቶ ፈርዶባቸዋል። አብዴልራውፍ አቡ ዛይድ መሀመድ ሀምዛ፣ መሀመድ መካዊ እብራሂም መሀመድ፣አብዴልበሲት አልሃጅ አልሃሳን ሀጅ ሀመድ፣እና መሀመድ ኦስማን ዩሲፍ መሀመድ በመስቀል በሞት እንዲቀጡ ተፈረደባቸው። ነገር ግን ከፍርዱ ብያኔ በኋላ ከአንድ ዓመት በኋላ በሱዳን የኮበር እስር ቤት አመለጡ። መሀመድ በግንቦት2011 በሶማሊያ እንደሞተ ተዘግቦአል። አብዴልራውፍ እንደገና በሱዳን ባለሥልጣናት ተማርኮአል። መካዊና አብዴልበሲት እንዳመለጡ ቀርተዋል።

አብዴልረሃማን አባስ ረህማን፣ዕድሜው 39፣በጁባ፣ሱዳን ነበረ የተወለደው እርሱም በዳርፉር፣ሱዳን ከየUSAID የአደጋ ዕርዳታ ምላሽ ቡድን አባላት አንዱ ሆኖ በUSAID ሥራውን በ2004 ዓ ም ጀመረ። እርሱም በካርቱም፣በህዳር 2005፣የUSAID/ሱዳን ተልዕኮ በሾፌርነት ተቀጠረ።

ጆን ግራንቪል፣33፣ከቡፋሎ፣ንው ዮርክ ነበረ። እርሱም በሱዳን በUSAID የዲሞክራሲና የመንግሥት አገዛዝ መርኃ ግብር፣ከሃያ ዓመታት በላይ በጦርነት ተለይቶ ለቀረው ለደቡብ ሱዳን አካባቢ፣ለዜጎች ስለ መብቶቻቸው ለማሳወቅና ለምርጫዎች እንዲዘጋጁ ዘንድ ለማገዝ በሺህ የሚቆጠሩትን በጸሀይ ኃይል የሚሠሩትን ራዲዮዎችን በማከፋፈል በመርዳት ከሦሥት ዓመት በላይ ሠርቶአል። ግራንቪል ከ1997 እስከ 1999 ድረስ በካሜሩን የሰላም ሠራዊት (Peace Corps) ፈቃደኛ ሠራተኛ ሆኖ አገልግሎአል እና ከዚያም በካሜሩን ገለልተኛ የሆነ ምርምር ለማካሄድ የ”Fulbright fellowship” ተቀብሎአል።

ሰለባዎች

የ--- ፎቶ ጆን ግራንቪል
ጆን ግራንቪል
የ--- ፎቶ አብዴልረሃማን አባስ ረህማን፣ዕድሜው
አብዴልረሃማን አባስ ረህማን፣ዕድሜው