የሚፈለጉ
ፍትህ የሚያመጣ መረጃ…

ፉአድ ሹክር (Fuad Shukr)

እስከ $5 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚደርስ ወሮታ

ፉአድ ሹክር በወታደራዊ ጉዳዮች ላይ ለሂዝቦላ ጠቅላይ ጸሐፊ ለሆነው ለሃሰን ናስራላ የረጅም ጊዜ አንጋፋ አማካሪ ነው። ሹክር በደቡብ ሊባኖስ የህዝቦላ ኃይሎች የወታደራዊ አሻዥ የሆነ አንጋፋ የሂዝቦላ ወታደር ነው። እርሱ የህዝቦላ ከሁሉ እጅግ ከፍተኛ የሆነ ወታደራዊ አካል፣ የጂሃድ ምክር ቤት አገልጋይ ነው።

ሹክር ለህዝቦላና በሂዝቦላ ፈንታ የሚያደርጋቸው ድርጊቶች ከ30 ዓመታት በላይ ዘልቀዋል። እርሱም በቅርቡ ለሞተው ለህዝቦላ አዛዥ ለሆነው ለእማድ ሙግኒያህ የቅርብ ባልደረባ ነበረ። ሹክር በእ ኤ አ በጥቅምት 23 ቀን 1983 ዓ ም፣በቤሩት፣ሊባኖስ በአሜሪካ የባህር ኃይል ሠፈሮች ጥቃት አድርሶ 241 የአሜሪካ አገልግሎት ሰጭዎችን የገደለውን ቦምብ በማቀድና በማስፈጸም ማዕከላዊ ሚና ተጫውቶአል።