የሚፈለጉ
ፍትህ የሚያመጣ መረጃ…

ፉአድ መሀመድ ከላፍ

እስከ $5 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚደርስ ወሮታ

ፉአድ መሀመድ ከላፍ ( ፉአድ ሾንጌል) በግንቦት 2008 ለአልሸባብ የገንዘብ ድጋፍ አመቻችቶአል፣እርሱም በክስማዩ ፣ሶማሊያ በመስጊድ ለአልሸባብ ሁለት የገንዘብ ማሰባሰቢያ ድርጊቶችን አስነድቶአል። በሚያዚያ፣2008 ከላፍና ሌሎች በርካታ ግለሰቦች በሞቃዲሾ፣ሶማሊያ በኢትዮጵያ ጣቢያዎችና በፌዴራሉን የሽግግር መንግሥት (TGF) ተሽከርካሪ- ወለድ የሚፈነዳ መሳሪያ ላይ አሰማርተዋል። በግንቦት 2008፣ከላፍና አንድ የተዋጊ ቡድኖች በሞቃዲሾ የፖሊስ ጣቢያን አጥቅተውና ማርከው፣ብዙ ወታደሮችን ገድለዋል፣እና አቁስለዋልም። በሚያዚያ 2010፣ በሶማሊያ ከላፍ አመጽ በማነሳሳትና ለደህንነት ማሽቆልቆል አስተዋጽኦ በማድረጉ የአሜሪካ የገንዘብ ሚንስቴር በሥራ መመሪያ ትዕዛዘ (Executive Order) 13536.አው መሀመድን በልዩ ሁኔታ ፈርጆታል።

አልሸባብ በ2006 አጋማሽ ደቡብ ሶማሊያ የተቆጣጠረው የሶማሊያ እስላማዊ ፍ/ቤቶች የወታደራዊ ክንፍ ነበረ። አልሸባብ አመጸኛ ተግባሩን በደቡብና በማዕከላዊ ሶማሊያ ቀጥሎበታል። ቡድኑ፣ በዋናኛው የሶማሊያ ማዕከላዊ መንግስትንና የሶማሊያ ፌዴራሉን የሽግግር መንግሥት የሚደግፉትን ኢላማ በማድረግ በደቡብና በማዕከላዊ ሶማሊያ የተለያዩ የአጥፍቶ ጠፊ ቦምብ ጥቃቶች ጨምሮ በርካታ የቦምብ ድብደባ እንደካሄደ ኃላፊነቱ ወስዶአል። አልሸባብ በ2008 በሰሜን ሶማሊያ በሁለት ከተማዎች ኢላማዎች አድርጎ ቢያንስ 26 ሰዎችን ገድሎ ሌሎች 29 ሰዎችን ላቆሰሉ በአንድ ጊዜ ለአምስት ለተቀነባበሩ የአጥፍቶ ጠፊ የቦምብ ጥቃቶች ተጠያቂ ሊሆን ይችላል። አልሸባብ በሀምሌ 11፣2010 በካምፓላ፣ኡጋንዳ አንድ አሜሪካዊን ጨምሮ ከ70 ሰዎች በላይ ለገደለው ለመንታ የአጥፍቶ ጠፊ የቦምብ ፍንዳታ ተጠያቂ ነበረ። ቡድኑ የሶማሊያ የሰላም አቀንቃኞችን፣ዓለም አቀፍ የዕርዳታ ሠራተኞችን፣በርካታ የሲቭል ማህበረሰብ ተዋቂ ሰዎችንና ጋዜጠኞችን ለመግደሉ ተጠያቂ ነው። በየካቲት 2012፣አልሸባብና አልቀይዳ መደበኛ ትብብራቸውን ይፋ አድርገዋል።

የአሜሪካ የገንዘብ ሚንስቴር፣በክፍል 219 በእምግሬሽንና የዜግነት ህግ በየካቲት 26፣2008 (እንደተስተካከለው) በሥራ መመሪያ ትዕዛዘ (Executive Order) 13224. መሠረት በየካቲት 29፣2008 አል ሸባብን በተለየ ሁኔታ ዓለም አቀፍ አሸባሪ ድርጅትእንደ ሆነ ፈርጆታል።