የሚፈለጉ
ፍትህ የሚያመጣ መረጃ…

ፋሩክ አል-ሱሪ።

እስከ $5 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚደርስ ወሮታ

ፋሩክ አል ሱሪ የአሸባሪው ድርጅት ሁራስ አል ዲን (HAD) መሪ ነው። አል-ሱሪ ለአስርተ ዓመታት በአሸባሪ ድርጅት ውስጥ ንቁ ሆኖ የቆየው የአልቃይዳ (AQ) የቀድሞ አባል ነው። እ.አ.አ. በ 1990 ዎቹ በአፍጋኒስታን ውስጥ ከAQ መሪ ክሆኑት ከሲፍ አል አድል ጋር የፓራሚሊታሪ አሰልጣኝ ነበረ፣ እንዲሁም ከ2003 እስከ 2005 ባለው ጊዜ ውስጥ በኢራቅ ውስጥ ለAQ ተዋጊዎችን አሰልጥኖአል፡፡ አል-ሱሪ ከዚህ በፊት እ.ኤ.አ. ከ2009 እስከ 2013 ድረስ በሊባኖስ ውስጥ በቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን ከዚያ በኋላ የአል ኑስራ ግምባር የጦር አዛዥ ሆነ፡፡ እ.ኤ.አ. በ2016 ከአል ኑስራ ግንባር ወጣ፡፡

እ.ኤ.አ. መስከረም 10 ቀን 2019 የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር አል-ሱሪን በሥራ አስፈፃሚ ትእዛዝ 13224 መሰረት በልዩ ሁኔታ የዓለም አቀፍ አሸባሪ ብሎ ፈርጆታል፡፡

ሁራስ አል-ዲን ብዙ አንጃዎች ከሃያት ታሂር አል-ሻም (HTS) ከተገነጠሉ በኋላ በ2018 መጀመሪያ ላይ በሶሪያ ውስጥ ብቅ ያለው ቡድን ነው፡፡ አል-ሱሪን ጨምሮ የHAD አመራር ለAQ እና ለመሪው ለአይማን አል-ዛዋሪ ታማኝ ነው፡፡

የተጨማሪ ፎቶ

ፋሩክ አል-ሱሪ።
Salman Raouf Salman - Spanish