የሚፈለጉ
ፍትህ የሚያመጣ መረጃ…

ፋቂር ቤን አብደአልአዚዝ ቡሶራ

እስከ $5 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚደርስ ወሮታ

ፋቂር ቡሶራ, ከዚህ ሌላ አቡ ዩሱፍ አል ቱኒዚ ተብሎ የሚታወቅ ዜግነቱ ቱኒዚያዊ የሆነ ከአሸባሪ ፅንፈኛ እስላማዊያን ጋር ከፍተኛ ግንኙነት ያለው ሠው ነው፡፡ በአጥፍቶ መጥፋት ሰማእት ለመሆን ያለውን ፍላጎት በግልፅ ያሳወቀ በአልቃኢዳ የሰለጠነ አሸባሪ ነው፡፡ ቦሶራ በሽብር ተጠርጣሪ የሆነው ቱኒዚያዊ የአብደራውፍ ጅዴይ ጓደኛ ሲሆን ከዚህ በፊት አብረው ተጉዘው ያውቃሉ፡፡

ቦሶራ ፈረንሳይ ውስጥ ለመኖር በ1988 ውስጥ የትውልድ ሃገሩን ቱኒዚያን ለቋል፡፡ በ1991 ውስጥ ፈረንሳይን በመልቀቅ ወደ ሞንትሪያል፣ካናዳ ተሠዷል፡፡ በ1990ዎቹ ውስጥ ከካናዳ ወደ ቱኒዚያ በተደጋጋሚ ተመላልሷል፡፡ ከዚያም 1999 ውስጥ የካናዳን ዜግነት ያገኘ ሲሆን ካናዳ ውስጥ በነበረበት ወቅት አምልኮቱን ምንትራያል በሚገኘው የአሱና መስጊድ ይከታተል ነበር፡፡

ቦሶራ በ1999 ውስጥ ካናዳን ለቋል፡፡ ምናልባትም ከ1999 – 2000 በነበረው ጊዜ ወደ አፍጋኒስታን ከአንድ ጊዜ በላይ ተጉዟል፡፡ አፍጋኒስታን ወስጥ እያለ በአልቃኢዳ ሠልጥኖ በማከታተል ወደ ካናዳ ተመልሷል፡፡

ቦሰራ ወደ ካናዳ ወይም ወደ አሜሪካ ተመልሶ በሽብር ጥቃት ላይ ተሳታፊ ለመሆን ሙከራ እንዳያደርግ አሁንም ባለስልጣናት ስጋት አላቸው:: ምናልባትም በከፍተኛ ህመም ተጠቅቶ እጅግ በጣም በከፋ የህመም ደረጃ እና በክብደት መቀነስና የአካላዊ ቅርፅ መቀየር ላይ ሊገኝ ይችላል፡፡