የሽብርተኝነት ድርጊቶች
መረጃ በ ...

በዳንኤል ፐርል ላይ የተፈጸመ ጠለፋ እና ግድያ

ካራቺ፣ ፓኪስታን | እ.አ.አ ጥር 23፣ 2002

በጥር 23 ቀን 2002 ዳንኤል ፐርል በፖኪስታን ካራቺ በአሸባሪዎች ተጠልፏል፡፡ ፐርል የዎል ስትሪት መጽሔት ሪፖርተር ነው፡፡ በወቅቱ ፐርል ጫማው ውስጥ ቦምብ ደብቆ አትላንቲክን በሚያቋርጥ አይሮፕላን ውስጥ ለማፈንዳት ሙከራ ስላደረገው ሪቻርድ ሪድ ይከታተል ነበር፡፡.

በየካቲት 21 ቀን 2002 ዳንኤል ፐርል ሲገደል በኢንተርኔት በወጣ ቪዲዮ ላይ ታየ:: የሟች ፐርል የሰውነት አካል ሜይ ላይ በግንቦት ተገኝቶ ወደ አሜሪካ ተመልሷል፡፡.

ከአንድ ወር በኋላ አህመድ ኦማር ሰይድ ሸክ እና ሶስት ሌሎች ተጠርጣሪዎች በፐርል ጠለፋና ግድያ ወንጀል ውስጥ በነበራቸው ተሳትፎ ተከሰዋል፡፡ በሃምሌ 15 ቀን 2002 እነርሱ ፖኪስታን ውስጥ ቅጣት የተላለፈባቸው ሲሆን በሸክ ላይ የሞት ፍርድ ተበይኖበታል፡፡.

ወሮታ ለፍትህ ፕሮግራም ለዚህ ጥቃት ተጠያቂ የሆኑ ሰዎችን ወደ ፍትህ ለማቅረብ የሚያስችሉ መረጃዎችን ለሚሠጡ ሰዎች እስከ 1 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚደርስ ወሮታ ያበረክታል፡፡.