የሚፈለጉ
ፍትህ የሚያመጣ መረጃ…

ሴሚል ባይኪ

እስከ $4 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚደርስ ወሮታ

ሴሚል ባይኪ የPKK ሥራ አስፈጻሚ አባል፣ መስራች አባልና አንጋፋ መሪ ነው፡፡ ባይክ በገንዘብ ሚኒስቴር የተፈረጀበት ነው፡፡

የኩርዲስታን ሰራተኞች ፓርቲ (PKK)፣ በተጨማሪም ኮንግራ-ጌል በመባል የሚታወቀው በአካባቢው ንቁ የሆነ የአሸባሪዎች ድርጅት እና በዩኤስ የውጭ አሸባሪ ድርጅት (FTO) እንደሆነ የተፈረጀበት ድርጅት ነው ፡፡ ፒ ኬ ኬ PKK የቱርክ መንግስት ባለስልጣናትን፣ ፖሊስ እና የፀጥታ ኃይሎችን አነጣጥሮአል እና እና ሲቪሎችን በጅምላ አቁስሎአል እና ገድሏል፡፡ ፒኬኬ የጦር መሣሪያዎችን እና ቁሳቁሶችን ለማግኘት በአውሮፓ ውስጥ ያለውን አውታረመረብ እና የወንጀል እንቅስቃሴዎችን ይጠቀማል፡፡ PKK የአጥፍቶ ጠፊ ቦምቦችን፣ እቤት ውስጥ የተሰሩ የተሽከርካሪዎችን ፈንጂ (VBIEDs) እና ሌሎች ጅምላ የሽብርተኝነት ዘዴዎችን ተጠቅሟል፡፡ PKK ደግሞ ወጣቶችን መልምሎ ያስተምራል፣ አንዳንዴ በጠለፋ፣ ተዋጊዎች አድርጎ ይቀጥራቸዋል፡፡ እ.ኤ.አ በ1993 PKK አሜሪካን ጨምሮ 19 ምዕራባውያንን ማረኩ እና በ1995 ደግሞ PKK ሁለት አሜሪካውያን በቦምብ ጎድቶአል፡፡

እ.ኤ.አ. በ 2015 እና 2016 ላይ PKK በቱርክ፣ በኤጂያንና እና በሜዲትራኒያን ባህር ዳርቻዎች ላይ፣ በከተማ ዙሪያ ማእከሎች እና በቱሪስት ቦታዎች ላይ ጥቃቶችን አስፍቶአል፡፡ በነሐሴ ወር 2016፣ ቡድኑ በስርናክ ፖሊስ ዋና መሥሪያ ቤት ላይ በመኪና ላይ የቦንብ ጥቃት አካሄዶ 11 ሰዎችን መግደሉንና እና ከ70 በላይ የሚሆኑትን ማቁሰሉን ተናግሮአል፡፡ እ.ኤ.አ. በሰኔ 2017፣ PKK በቱርክ በደቡብ ምስራቅ ውስጥ አንድ የጦር ሰራዊት ተሽከርካሪዎች ላይ ጥቃት ሰንዝሮ ከ20 በላይ ወታደሮችን ገድሏል፡፡ ከ2015 ጀምሮ፣ ቡድኑ ከ 1,200 በላይ የቱርክ የደህንነት ሰራተኞችንና እና ሲቪሎችን ለሞት ዳርጓል፡፡

የተጨማሪ ፎቶ

PKK Poster - English
PKK - Kurdish Poster
PKK - Turkish Poster