የሽብርተኝነት ድርጊቶች
መረጃ በ ...

በቱሪስቶች ላይ የተፈጸመ ጥቃት

ቢዊንዲ ፓርክ፣ ኡጋንዳ | መጋቢት 1፣1999

በመጋቢት 1 ቀን 1999 በኡጋንዳ በዊንዲ ብሔራዊ ፖርክ 100 የኢንተርሃሞይ ወታደሮች ባልታጠቁ ቱሪስቶች እና በአስጐብኝዎቻቸው ላይ ጥቃት ፈፀሙ፡፡ ኢንተርሃሞይ ማለት በ1994 በሪሩዋንዳ የዘር ማጥፋት ወንጀል ቱትሲዎችን ለማጥፋት በሁቱ ወጣት ወንዶች የተቋቋመ ወታደራዊ ድርጅት ነው፡፡.

በብውንዲ ፖርክ ጥቃት በርካታ ቱሪስቶች ጥቃትና ምርኮ የደረሰባቸው ሲሆን ወደ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በእግራቸው እንዲሄዱ ተገደዋል፡፡ ፖልሮስ ዋጋባ የተባለ ኡጋንዳዊ በሕይወት እያለ አቃጥለውታል፡፡ አሜሪካውያኑ ሱዛን ሚለርና ሮበርት ሆብነርን ጨምሮ ስምንት ጉዳተኞች ለሞት ሊዳርጋቸው የሚችል ድብደባ ተፈጽሞባቸዋል፡፡.

በዚህ ጥቃት ብዙ የቱሪስቶቹ ንብረት የተሰረቀ ሲሆን, ከተሰረቁት ንብረቶች መሃከል የአሜሪካ ፖስፖርት የአሜሪካ የመንጃ ፈቃድ, የሴቶች ሲቲዘን የውሃ ውስጥ ጠለቃ ሰዓት, እና የቶ ሺባ ፖርቶጎ ላፕቶፕ ኮምፒዩተር ይገኙባቸዋል፡፡.

ወሮታ ለፍትህ ፕሮግራም ለዚህ ጥቃት ተጠያቂ የሆኑ ሰዎችን ወደ ፍትህ ለማቅረብ የሚያስችሉ መረጃዎችን ለሚሠጡ ሰዎች እስከ 1 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚደርስ ወሮታ ያበረክታል፡፡.