የሽብርተኝነት ድርጊቶች
መረጃ በ ...

በቤንጋዚ ፤ ሊቢያ በአሜሪካ ልዩ ተልዕኮ ግቢና በተቀጽላው ላይ የተፈጸመ የአሸባሪዎች ጥቃት

የአሸባሪዎች ጥቃት|መስከረም 11-1, 2012 ([በዚህ ጽሁፍ የተጠቀሱት ቀኖችና ዓ ም የተገለጹት እ ኤ አ ነው])።

በመስከረም 11-12, 2012 ፤ አራት አሜሪካዊያን — ጆን ክርስቶፌር እስቲቬንስ በሊቢያ የአሜሪካ አምባሳደር ፤ ሲአን እስሚዝ ፤ የውጭ አገልግሎት መረጃ አያያዝ መኮንን ፤ እና የመከላከያ ደህንነት ባለሞያዎች ፤  ግሌን አንቶኒ ዶሄርቲና ታይሮን እስኖዴን ዉድስ — በበቤንጋዚ ፤ ሊቢያ በአሜሪካ ልዩ ተልዕኮ ግቢና በተቀጽላው ላይ  በአሸባሪዎች በተፈጸመ ጥቃት ተገደሉ።    በቃጠሎ ፤ በመተሪያሶች ፤ በሮኬት ተስፈንጣሪ የእጅ ቦምቦች ግሪኔዶች (RPGs) ፤ በጠብመንጃዎች እና በቤንጋዚ በሚገኙት በሁለት የአሜሪካ ግቢ ፣ እንዲሁም በሁለቱም ግቢዎች መካከል በመንገድ ላይ በሚገኙት ሠራተኞች ላይ የተለያዩ ጥቃቶች ተፈጽመዋል።  በተጨማሪ ፤ ጥቃቶቹ ሁለት የአሜሪካ ሠራተኞች አቁስለዋል፤ ሦሥት የሊቢያ የኮንትራት ዘበኞችን አቁስለዋል ፤ እና ሁለቱም ግቢዎች እንዲጠፉና እንዲተው አስደርገዋል።

ወሮታ ለፍትህ ፕሮግራም ለዚህ ጥቃት ተጠያቂ የሆኑ ሰዎችን ወደ ፍትህ ለማቅረብ የሚያስችሉ መረጃዎችን ለሚሠጡ ሰዎች እስከ 10 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚደርስ ወሮታ ያበረክታል፡፡.

አምባሰደር ጆን ክርስቶፌር እስቲቬንስ፣ዕድሜአቸው 52፣ በሰሜን ካልፎርኒያ ነበረ የተወለዱት፤ እና በውጭ አገልግሎት ሥራቸውን የጀመሩት በ1991 ዓ ም ነበረ።  አምባሰደር ጆን ክርስቶፌር እስቲቬንስ በበርካታ የውጭ አገር ሥራዎች ሠርተዋል እና ከ2007 እስከ 2009 በሊቢያ የተልዕኮው ምክትል ኃላፊ ነበሩ።  አምባሳደር እስቲቬንስ፣ ከመጋቢት 2011 እስከ ህዳር 2011 ለሊቢያ የሽግግር ምክር ቤት ልዩ ተወካይ ሆነው አገልግለዋል ፤ እና ለለቢያ የአሜሪካ አምባሰደር ሆነው በግንቦት 2012 ትሪፖሊ ደርሰዋል።   በውጭ አገልግሎት ከመግባታቸው በፊት ፤ አምባሰደር እስቲቬንስ በዋሽንግተን ዲ ሲ የዓለም አቀፍ ንግድ ጠበቃ ነበሩ እና ከዚያ በፊት ከ1983 እስከ 1985 ድረስ በሞሮኮ የፒስ ኮፕስ ፈቃደኛ የእንግሊዝኛ መምህር ነበሩ።   የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሂሊያሪ ሮዳሃም ክልንቶን አምባሰደር እስቲቬንስን ፤ ” ጀግናና ጥሩ ሰው እና የተካኑ ድፕሎማት ፤ እና አሜሪካዊ ጀግና ናቸው ” ብለዋል።

ሲአን እስሚዝ፣ ዕድሜቸው 34 ፤ የተወለዱት በሳንዲያጎ ካልፎርኒያ ሆኖ ፤ በ1995 በአየር ኃይል ተቀጥረው የምድር ራዲዮ ጥገና ባለሞያና የሃምሳ አለቃ ነበሩ።  እስሚዝ በ2002 በውጭ አገልግሎት የውጭ አገልግሎት መረጃ አያያዝ መኮንን ሆነው ገብተው፤ ባግዳድ ፤ ፕሪቶሪያ ፤ ሞንትሪያል፤ እና ሄግ ጨምሮ በተለያዩ የውጭ አገር ሥራዎች አገልግለዋል።  እስሚዝ ለአሜሪካ ልዩ ተልዕኮ የመገናኛዎችና የአያያዝ ድጋፍ ለመስጠት በ2012 ወደ ቤንጋዚ ፤ ሊቢያ ተጓዙ።

ግሌን አንቶኒ ዶሄርቲ ፤ ዕድሜአቸው 42 ፤ የተወለዱት በዊንቼስቴር ፤ ማሳቹሴትስ ሆኖ ፤ በ1995 በአሜሪካ የባህር ኃይል “SEAL” ተቀጥረው በሥራቸው ወቅት በኢራቅና አፍጋኒስታን አገልግለዋል።   በባህር ኃይል ከመቀጠራቸው በፊት ፤ ዶሄርቲ የሰለጠኑ የሸርተቴ አስተማሪ ነበሩ ፤ የበረራ ትምህርት ተምረዋል ፤ እና ልምድ የነበራቸው የበረራ አሰልጣኝና የህክምና ዕርዳታ አሰልጣኝ ነበሩ። በ2005 ፤ ዶሄርቲ በውጭ አገር ለሚገኙ የአሜሪካ ባለሥልጣኖች የደህንነት አገልግሎት ለሚያበረክት የግል ድርጅት ሠርተዋል።  ዶሄርቲ ለአሜሪካ ልዩ ተልዕኮ ደህንነት ለማቅረብ በመስከረም 2012 ወደ ቤንጋዚ ፤ ሊቢያ ተጓዙ።

ታይሮን እስኖዴን ዉድስ ፤ ዕድሜአቸው 41 ፤ የተወለዱት በፖርትላንድ ኦሬጎን ሆኖ፤ የባህር ኃይል “SEAL” ሆነው በሶማሊያ ፤ ኢራቅና አፍጋኒስታን ብዙ ተጉዘዋል።  ውድስ ሬጅስቴርድ ነርስና የተመሰከረላቸው በህክምና የሚረዱ ነበሩ።   በ2010 ፤ ውዲስ በግል የደህንነት ድርጅት አማካይነት  በውጭ አገር ለሚገኙ የአሜሪካ ባለሥልጣኖች የደህንነት አገልግሎት ማቅረብ ጀመሩ።  ውዲስ ለአሜሪካ ልዩ ተልዕኮ ደህንነት ለማቅረብ በ2012 ወደ ቤንጋዚ ፤ ሊቢያ ተጓዙ።

ሰለባዎች

የ ጆን ክርስቶፌር እስቲቬንስ ፎቶ
ጆን ክርስቶፌር እስቲቬንስ
የ ሲአን እስሚዝ ፎቶ
ሲአን እስሚዝ
የ ግሌን አንቶኒ ዶሄርቲ ፎቶ
ግሌን አንቶኒ ዶሄርቲ
የ ታይሮን እስኖውዴን ዉድስ ፎቶ
ታይሮን እስኖውዴን ዉድስ