የሚፈለጉ
ፍትህ የሚያመጣ መረጃ…

አይማን አልዘዋሃሪ (Ayman al-Zawahiri)

እስከ $25 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚደርስ ወሮታ

አይማን አል – ዛዋህሪ የአሁኑ የአልቃይዳ አሽባሪ ቡድን መሪ ነው እና የቀድሞ የቀድሞ የግብጽ እስላማዊ ጅሃድ አባል ነበረ። እርሱም እ ኤ አ በነሐሴ 7 ቀን 1998 ዓ ም በኬንያና በታንዛኒያ በአሜሪካ ኤምባሲ ላይ ፈንድቶ 224 ሲቪሎችንና ከ5,000 በላይ ሌሎችን ላቆሰለው ለቦንብ ፍንዳታ ሚና በአሜሪካ ተከሶአል።

ከኡሳማ ቢን ላዴንና ከሌሎች አንጋፋ የአልቃይዳ አባላት ጋር ፣ አል – ዛዋህሪ በዩ ኤስ ኤስ ኮል በየመን በጥቅምት 12 ቀን 2000፣ 17 የአሜሪካ መርከበኞችን የገደለውንና ሌላ 39 ያቆሰለውን ጥቃት ለማሴሩና 19 የአልቃይዳ አሽባሪዎች አራት የንግድ ጄቶችን – ሁለቱ በኒው ዮርክ በዓለም በንግድ ማዕከል ፣ አንዱ በዋሽንግተን ዲ ሲ አካባቢ በፔንታጎን ፣ እና አረተኛው በፔንስልቫኒያ፣ ሸንክስቪል ማሳ ላይ ወድቆ ወደ 3000 የሚጠጉትን ሰዎች በገደለው ጠለፋና ክስከሳ በመስከረም 11 ቀን 2001 ጥቃቶችን በማቀነባበር በመርዳቱ ይታመናል።

አል – ዛዋህሪ አሁን ሰፊው የአልቃይዳ ማዕከል ተብለው የሚጠሩትን ትንሽ ግን ተዋቂ ነገር ግን አንጋፋ መሪዎችን እየመራ ነው ፣ አመራሩ በአፍጋኒስታንና በፓክስታን በነበረው የጸረ ሽብርተኝነት ግፊት እና ለአንዳንድ ላልረኩ አክራሪዎች አማራጭ ሆኖ በሚያገለግለው የኢራቅና ሌቫንት እስላማዊ መንግስት (ISIL) በመሳሰሉትና በሌሎች ድርጅቶች መነሳት ምክንያት ባለፉት ጥቂት ዓመታት የቡድኑ አንድነት ቀንሶአል። ቢሆንም ቅሉ ፣ በደቡብ እስያ ፣ በአፍሪካ ፣ እና በመካከለኛ ምሥራቅ የሚገኙት አልቃይዳና ሸሪኮቻቸው በአሜሪካና ውጭ አገር ባሉት የአሜሪካ ፍላጎቶች ላይ ጥቃቶችን ለማካሄድ ቆርጠው የተነሱ የማይበገሩ ድርጅቶች ሆነዋል።

አልቃይዳ ባለፉት በርካታ ዓመታት ብዙ ያልተሳኩ ጥቃቶችን በአሜሪካና በአውሮፓ ጭምር ሲያነጣጥር፣ አል – ዛዋህሪ መልዕክቶችን ማመዝገቡንና ማሰራጨቱን እየቀጠለ ነው። ይህም የሚያሳየው በዘላቂ የጸረ ሽብርተኝነት ግፊት አልቃይዳ አንዳንድ የጥቃት ዝግጅቶችን መቀጠል መቻሉን ነው እና በአሜሪካ ወይም በውጭ አገር ተጨማሪ ጥቃቶችን እያሴራ ሊሆን እንደሚችል ያሳያል።