የሚፈለጉ
ፍትህ የሚያመጣ መረጃ…

አህላም አህመድ አል- ታሚሚ

እስከ $5 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚደርስ ወሮታ

ደግሞ “ ካህልቲ” እና “ ሃላቲ” ተብላ የምትጠራው ዮርዳኖሳዊ ዜጋ የሆነችው፣ አህላም አህመድ አል- ታሚሚ ለሃማስ የምትሰራ አሸባሪ በመሆኗ ተፈርዶባታል።

እ ኤ አ በነሀሴ 9 ቀን 2001 ዓ ም ፣ አል- ታሚሚ ቦምብና የሃማስ አጥፎ ጠፊ ቦምብ አፈንጂን ህዝብ ወደ ሞላበት ወደ ኢየሩሳሌም ስባሮ ፕዜሪያ አጓጉዞለች። ቦምብ አፈንጂው ፈንጂውን አፈንድቶ፣ ሰባት ልጆችን ጨምሮ፣ 15 ሰዎችን ገድሎአል። በጥቃቱ ሁለት የአሜሪካ ዜጎችም ተገድለዋል – እርጉዝ የነበረች ዕድሜዋ 31 ዓመት የነበረ ከኒው ጄርሲ መምህርት የነበረች ጁዲት ሾሸና ግሪንባውም፣ እና ዕድሜዋ 15 ዓመት የነበረው ማልካ ቻና ሮዝ ተገድለዋል። አራት አሜሪካዊያንን ጨምሮ ከ20 በላይ ሌሎች ሰዎች ቆስለዋል። ለቦምቡ ጥቃት ሃማስ ኃላፊነቱን ወስዶአል።

እ ኤ አ በ2003 ፣ አል- ታሚሚ በእስራኤል ፍርድ ቤት በጥቃቱ በመሳተፏ ጥፋተኛ መሆኑን አመነ እና ቦምብ አፈንጂውን በማገዙ ለ16 የህይወት ዘመን እስረት ተፈርዶበታል። እርስዋም በእስራኤልና በሀማስ መካከል በተደረገው የእስረኞች ልውውጥ በጥቅምት 2011 ተለቃለች። በመጋቢት 14 ቀን፣ የአሜሪካ የፍትህ ሚንስቴር የወንጀል ክስ አጋልጦ አል- ታሚሚ እንድትታሰር ትዕዛዝ አወጣ እና በአሜሪካ ህግ መሰረት “ ከአሜሪካ ውጭ፣ ሞት ያስከተለውን በጅምላ አጥፊ የሆነ የጦር መሳሪያ ለመጠቀም በማሴሯ“ ክስ ተመሰርቶባታል። ” ኤፍ ቢ አይ ደግሞ አል- ታሚሚን በእጅጉ ከሚፈለጉ አሸባሪዎች ዝርዝር ውስጥ ጨምሮአታል እና “ መሳሪያ የታጠቀችና አደገኛ ” እንደሆነች ይገነዘባታል።

በኤፍ ቢ አይ መሠረት፣ በትርፍ ጊዜዋ የቴሌቪዥን ጋዜጠኛ የነበረች የቀድሞ ተማሪ አል- ታሚሚ በሃማስ ወታደራዊ ክንፍ ፈንታ ጥቃቶችን ለማካሄድ ቃል ገብታ ቦምብ አፈንጂውን ወደ ኢላማው በተሽከርካሪ አድርሳለች። የስባሮ ጥቃት ያቀደችና የጠነሰሰች አል- ታሚሚ፣ ቦታውን የመረጠችበት ምክንያት ሥራ የሚበዛበት ምግብ ቤት በመሆኑ ነበረ። ጥርጣሬን ለመቀነስ ፣ እርሷና አጥፍቶ ጠፊ ቦምብ አፈንጂው እንደ እሥራኤላዊያን ለበሱ፣ እና እርሷ እራሷ ቦምቡን በግታር ቦርሳ ከአንድ የዌስት ባንክ ከተማ ወደ ኢየሩሳሌም ደብቃ አጓጉዛለች።አል- ታሚሚ፣ ከጥቃቱ ከጥቂት ሳምንታት በፊት ለሙከራ ደግሞ ትንሽ እቤት ውስጥ የተሰራ ቦምብ በኢየሩሳሌም የሸቀጣ ሸቀጥ መደብር ማፈንዳቷንን አምናለች።

በእምግሬሽንና በብሄርተኝነት ህግ እና በ E.O. 13224 በልዩ ሁኔታ የውጭ አሸባሪ ድርጅት (SDGT) ሃማስ በውጭ ጉዳይ ሚንስቴር የውጭ አሸባሪ ድርጅት እንደሆነ (FTO) ተፈርጆበታል።

በ1993 በመካከለኛ ምሥራቅ የሰላም ስምምነቶች ተቃውሞ አመጽ ሽልማት ስጦታ አካል አል- ታሚሚን በዚህ ጥቃት ለነበራት ሚና ለፍርድ ወይም ለእስረት ለሚያቀርባት መረጃ የወሮታ ለፍትህ መርኃ ግብር እስከ $5 ሚሊዮን ድረስ ይሰጣል።

ተጨማሪ ፎቶዎች

ማልካ ቻና ሮዝ
ማልካ ቻና ሮዝ
ጁዲት ሾሸና ግሪንባውም
ጁዲት ሾሸና ግሪንባውም
የ2000 የእስባሮ ፕዜሪያ የቦምብ ጥቃት
የ2000 የእስባሮ ፕዜሪያ የቦምብ ጥቃት
አህላም አህመድ አል- ታሚሚ
አህላም አህመድ አል- ታሚሚ