የሚፈለጉ
ፍትህ የሚያመጣ መረጃ…

አቡበከር ሼካሁ

እስከ $7 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚደርስ ወሮታ

አቡበከር ሸካኡ ሼካኡ በተለምዶ በበለጠ ቦኮ ሃራም ተብሎ የሚታወቀው፣የጀማተሁ አል አል ሱና እል-ደዋቲ ዋል-ጅሃ ድ መሪ ነው።  ቦኮ ሃራም፣ ይኸውም “ የምዕራባዊያን ትምህርት የተከለከለ”ማለት ሲሆን፣የአሁኑን የናይጄሪያን መንግሥት ገልብጦ በእስላማዊ ህግ የሚተዳደር መንግሥት ለመመስረት የሚፈልግ ናይጄሪያዊ አሸባሪ ድርጅት ነው። ቡድኑ ከ1990ዎቹ ጀምሮ በተለያዩ መልኮች ይገኛል። የቦኮ ሃራምን የሽብርተኝነት ጥቃት አቅም ሊያጠናክር የሚችል በቦኮ ሃራምና፣ በእስላማዊ ማግሬብ ምድሮች በሚገኝ አልቀይዳ(AQIM)፣ አልሸበብ፣እና በአረብ ፔንንሱላ በሚገኘው አልቀይዳ መካከል ግንኙነቶች፣ስልጠና፣የጦር መሳሪያዎች ግንኙነት እንዳለ ይነገራል።

ሼከሁ ቀድሞ የቡድኑ ሁለተኛ አዛዥ ነበረ። በሀምሌ 2010፣ ሼከሁ ባይፈ የቦኮ ሃራምን መሪነቱን መጎናጸፉን አውጆ በነይጄሪያ በሚገኙት በምዕራባዊያን ፍላጎቶች ላይ ጥቃት ለመሰንዘር ዝቶአል። በኋላ በዚያው ወር፣ ሼከሁ ከአልቀይዳ ጋር ጋር አንድነት ለማጠናከርና የአሜሪካንን ለመጉዳት ሁለተኛ መግለጫ አውጥቶአል።በሼከሁ አመራር የቦኮ ሃራም የድርጊቱ ችሎታዎች አድገዋል።

ቡድኑ የመጀመሪያውን በመኪና የሚጠመዱ ፈንጂዎችን (IED) በሰኔ 2011 አፈንድቶአል፣ እና መከላከያ በሌለባቸው ኢላማዎች ላይ IEDዎን በጥቃቶችን በበለጠ ተጠቅሞአል። እ ኤ አ በነሀሴ 26፣2011 ቦኮ ሃራም በናይጄሪያ በአቡጃ በሚገኘው በተመድ ዋና ጽ/ቤት ያካሄደው የመኪና ላይ ጥቃት ቡድን በምዕራባዊያን ፍላጎቶች ላይ ያነጣጠረው የመጀመሪያ ገዳይ ድርጊት ነበረ።በጥቃቱ ቢያንስ 23 ሰዎች ተገድለው፣በተጨማሪ 80 ሰዎች ቆስለዋል። የቦኮ ሃራም ቃለ አቃባይ የተባለ ሰው ለጥቃቱ ኃላፊነቱን ወስዶአል እና ወደ ፊት የአሜሪካንንና የናይጄሪያ መንግስታት ፍላጎቶችን ለማጥቃት ቃል ገብቶአል።  

በአቡጃ በሚገኘው በናይጄሪያ ጋዜጣ ህንጻ ላይ የቦምብ ጥቃት ባደረሰ አንድ ሳምንት በማይሞላ ጊዜ ውስጥ፣በግንቦት 1፣2012 ቦኮ ሃራም በአሜሪካ ድምጽና ሳሃራ ሪፖርቴሮች በሚባል በንው ዮርክ የብዙሃን መገናኛ ድርጅት ጨምሮ በአገር ውስጥና በዓለም አቀፍ የዜና ማሳራጫዎች ላይ የበለጠውን ጥቃት ለመሰንዘር የቪድዮ መግለጫ አውጥቶአል።

በሼካው አመራር ቦኮሃራም በተከታታይ ወጣት ልጆችን አነጣጥሮአል። እ ኤ አ በሚያዚያ 14 ቀን 2014 ፣ ቦኮሃራም በሰሜን ናይጄሪያ ከሚገኘው ት/ቤታቸው ወደ 300 የሚጠጉትን ልጃ ገረዶች አፍኖ ወስዶአል። ከሦሥት ሳምንታት በኋላ በተለቀቀው የቪድዮ መልዕክት ፣ ሼካው ለአፈናው ኃላፊነቱን ወስዶአል፣ ልጃ ገረዶቹንም ች ባሮች ብሎ በመጥራት በገበያ እንደሚሸጣቸው ዝቶአል።

በሰኔ 21, 2012 በሥራ አፈጻጸም መመሪያ ትዕዛዝ 13224 መሠረት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር፣ ሼካሁን ልዩ የዓለም አቀፍ አሸባሪ አድርጎ ፈርጆታል።