የሚፈለጉ
ፍትህ የሚያመጣ መረጃ…

አቡ ኡባይዳ ድሬዬ (Abu Ubaidah (Direye))

እስከ $6 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚደርስ ወሮታ

አቡ ኡበይዳ፣ (ድርዬ) የአል- ሸባብ መሪ ነው። የአል- ሸባብ ቃል አቃባይ የሆነው፣ አህመድ አብዲ አው መሀመድ ፣ የቀድሞው ኤሚር አህመድ አብዲ አው – መሀመድ ( ጎዳኔ) ከሞተ በኋላ አቡ ኡበይዳ የቡድኑ መሪ እንደሆነ በመስከረም 6 ቀን 2014 አሳውቆአል። አቡ ኡበይዳ በጎዳኔ ሞት ጊዜ የጎዳኔ ሚስጢረኞች አካል ነበረ። በመስከረም 24 ቀን 2014 ( በዚህ ጽሁፍ የተጠቀሱት ቀናትና ዓ ም የተገለጹት እ ኤ አ ነው) በውሳኔ 1844 መሠረት የተመድ የጸጥታ ምክር ቤት በርሱ ላይ ማዕቀብ ጥሎአል።

እርሱ አል- ሸባብ ከሶማሊያ ብሄርተኛ እንቅስቃሴ የሚበልጥና አሊያም በአልቃይዳ ዓለም አቀፍ ጂሃድ አንድ ግንባር እንደሆነ ያምን በነበረው በጎዳኔ አመለካከት እንደሚመራ ይታመናል።

እሚር በመሆኑ ፣ የሶማሊያንና በአካባቢው የአሜሪካንን ሰላም ፣ ደህንነት ፣ እና መረጋጋት ስጋት ላይ በጣለው ለአል- ሸባብ ድርጊቶች አቡ ኡበይዳ በቀጥታ ኃላፊ ነው። ዕድሜው በአርባዎቹ ዓመታት ውስጥና በሶማሊያ የክስማዮ አካባቢ የድር ጎሳ አባል እንደሆነ ይታመናል።