የሚፈለጉ
ፍትህ የሚያመጣ መረጃ…

አቡ ባክር አል - ባግዳዲ (Abu Bakr al-Baghdadi)

እስከ $25 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚደርስ ወሮታ

ደግሞ አቡዱሃ በመባል የሚታወቀውአቡ ባክር አል- ባግዳዲ፣ ደግሞ “ አዋድ እብራሂም አ- አልባድሪ በመባል የሚታወቀው ፣ የአሸባሪ ድርጅት የኢራቅና ሌቫንት እስላማዊ መንግስት (ISIL) አንጋፋ መሪ ነው። እርሱ የሚገኝበትን ቦታ ፣ እርሱን ለማስያዝ፣ ወይም ለማስፈረድ የሚያደርሰውን መረጃ ለሚያቃብል ሰው የውጭ አገር ሚንስቴር $10 ሚሊዮን ዶላር ወሮታ ለመስጠት በ2011 ካሳወቀበት ጊዜ ጀምሮ አል- ባግዳዲ የሚያካሄደው ጥቃት በጣም ጨምሮአል ። በሰኔ 2014፣ ISIL (ዳኤሽ በመባል የሚታወቀው)የሶሪያንና የኢራቅን ከፊል ተቆጣጥሮአል እና የእስላማዊ ካሊ ፌት ማቋቋሙን፣ እና አል- ባግዳዲን ካልፈው እንዳደረገ በአዋጅ አሳውቆአል። በቅርብ ዓመታት ውስጥ፣ ISIL በመላው ዓለም የጂሃድስት ቡድኖችንና አክራሪ የተደረጉ ግለሰቦችን ታማኝነት አግኝቶአል፣ እና በአሜሪካ ላይ ጥቃቶችን አነሳስቶአል።

በአል- ባግዳዲ አመራር፣ ISIL ከጀፓን ፣ ከእንግሊዝና ከአሜሪካ ጭምር በርካታ የሲቪል ምርኮኞች አሳቃቂ ግድያ ጭምር በመካከለኛ ምሥራቅ በሺዎች ለሚቆጠሩት ሲቪሎች ሞት ተጠያቂ ነው ። አል- ባግዳዲ ፣ በሺህ የሚቆጠሩትን የአገሩን ዜጎች በመግደል፣ከ2011 ጀምሮ ለበርካታ አሸባሪ ጥቃቶች ኃላፊነት ወስዶአል። ቡድኑ እራሱን ከሰየመው ካሊፌት ድንባሮች አልፎ የአሸባሪነት ጥቃቶችን አካሄዶአል። በህዳር 2015 ፣ ሁለት የISIL የአጥፍቶ ጠፊ የቦምብ ፍንዳታዎች በቤሩት 43 ገድለው 239 አቁስለዋል። በዚያው ወር ፣ ISIL በፓሪስ ሰባት የተቀነባበሩ ጥቃቶችን አካሂዶ – ቢያንስ 130 ገድሎ ከ350 በላይ አቁስሎአል። በመጋቢት 2016 ፣ አሸባሪዎች በብሩሴልስ ቢያንስ 34 ሰዎችን ገድለዋል – አራት የአሜሪካ ዜጎችን ጭምር – እና ከ270 በላይ የሆኑትን አቁሰለዋል።

አል- ባግዳዲ በሥራ መመሪያ 13224 መሰረት በውጭ ጒዳይ ሚኒስቴር በልዪ ሁኔታ የተመደበ ዓለም አቀፍ አሸባሪ ( Specially Designated Global Terrorist (SDGT) እንደሆነ ተወስኖበታል። እርሱ ደግሞ በተመድ የጸጥታ ምክር ቤት የISIL (ዳኤሽ) እና የአልቃይዳ ማእቀቦች ኮሚቴ ውስጥ ተዘርዝሮአል።

የተጨማሪ ፎቶ

Baghdadi Poster 1 - English
Photo of Abu Bakr al-Baghdadi