የሚፈለጉ
ፍትህ የሚያመጣ መረጃ…

አቡ - ሙሀመድ አል - ሽማሊ (Abu-Muhammad al-Shimali)

እስከ $5 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚደርስ ወሮታ

በተሻለ ሁኔታ አቡ – ሙሀመድ አል – ሽማሊ በመባል የሚታወቀው ታራድ አል-ጀርባ ቀድሞ አል-ቃይዳ በኢራቅ ተብሎ ለሚታወቀው የኢራቅና የሌቫንት እስላማዊ መንግሥት (Islamic State of Iraq and the Levant (ISIL) ከ2005 ጀምሮ አንጋፋ የድንበር ኃላፊ ነው። እርሱ አሁን በISIL የእምግሬሽንና ሎጂስትካዊ ኮሚቴ ቁልፍ ባለሥልጣን ነው፣ እና የውጭ አገር አሸባሪ ተዋጊዎችን በዋናኛው በጋዚያንቴፕ፣ ቱርክ፣ እና በሶሪያ በISIL ቁጥጥር ሥር ወዳለችው ወደ ጀረቡሉስ ከተማ ድንበር ጉዞ በማመቻቸት ኃላፊ ነው። የእምግሬሽንና ሎጂስትካዊ ኮሚቴና አል-ሽማሊ የኮንትሮባንድ ድርጊቶችን ፣ የገንዘብ ማስተላለፍ፣ እና የሎጂስትክ እንቅስቃሴዎችን ከአውሮፓ፣ ከሰሜን አፍሪቃ፣ እና ከአረብ ባህረ ሰላጤ ወደ ሶሪያና ኢራቅ ያቀነባብራሉ። በ2014 ፣ ከአውስትራሊያ፣ አውሮፓ ፣ እና ከመካከለኛ ምሥራቅ የተውጣጡትን የISIL ተዋጊዎችን ጉዞ ከቱርክ ወደ ሶሪያ አል-ሽማሊ አመቻችቶአል ፣ እና በሶሪያ፣ አዛዝ ለአዲስ ምልምሎች የISIL ማቀነባበሪያ ማዕከል አስተዳድሮአል ።

አሜሪካና ከ60 በላይ ዓለም አቀፍ ህብረት ተባባሪዎች ISILን ለማዋረድና ፣ በመጨረሻም ድል ለመንሳት ቆርጠው ተነስተዋል። ይህንን ዓላማ ማሳካት በጋራ በርካታ የማጠናከሪያ ጥረት መስመሮችን ይፈልጋል። ከህብረቱ ቁልፍ የማጠናከሪያ ጥረት መስመሮች አንዱ የውጭ አገር አሸባሪ ተዋጊዎችን መፍሰስ ማስቆም ነው። ይህ አቀራረብ የሀገር ውስጥ ዳህንነት፣ የህግ ማስከበሪያን፣ የፍትህ ዘርፍ ፣ ስለላ ፣ ዲፕሎማሲያዊ ፣ ወታደራዊ፣ የአቅም ግንባታ ፣ እና የመረጃ ልውውጥ ጥረቶችን ባንድነት ያመጣል።

ከ100 አገሮች በላይ የተውጣጡ ከ25,000 በላይ የውጭ አገር አሸባሪ ተዋጊዎች ወደ ኢራቅና ሶሪያ ተጉዘዋል። በኢራቅና በሶሪያ የሚገኙ የጦር ሜዳዎች የውጊያ ልምድ ፣ የጦር መሳሪዎችንና የፈንጂዎችን ሥልጠና፣ እና ምዕራባዊያንን ለማጥቃት በእቅድ ላይ ሊኖሩ የሚችሉትን የአሸባሪ መረቦችን እንዲያገኙ አድርጎአቸዋል። የጋራ የውጭ አገር አሸባሪ ተዋጊዎች ስጋት ፣ የተዋጊዎችን መፍሰስና በመጨራሻም ISILን ለማሸነፍ ያለውን ሁሉ ነገር የሚያጠናክር ከአሜሪካ የፌዴራል መሥሪያ ቤቶችና ከዓለም አቀፍ ተባባሪዎች ጋር እንዲያውም የቀረበ ትብብር እንዲኖር አድርጎአል።