በጅምላ አጥፊ የጦር መሳሪያዎች

በጅምላ አጥፊ የጦር መሳሪያዎችን ለመያዝና ለመጠቀም ፍላጐት ያላቸው አሸባሪዎች መኖራቸው በአለም አቀፍ ሰላምና ደህንነት ላይ ከባድ አደጋን ደቅኗል፡፡ በጅምላ አጥፊ የጦር መሳሪያዎ ች ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሠላማዊ ሰዎችን ሊገድሉና ከአካባቢ የአደጋ ምላሽ ሰጪ ክፍሎች አቅም በላይ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ “>በጅምላ አጥፊ የጦር ማሳሪያዎች የኑክሌር፣ የኬሚካል፣ የባዮሎጂካል እና የራዲዮሎጂካል ጦር መሳሪያዎች እንዲሁም ከፍተኛ ውድመት የማድረስ አቅም ያላቸው ከፍተኛ ቦ ምቦችን ያጠቃልላሉ፡፡.

ዩናይትድ ስቴትስ እነዚህ አሸባሪዎች በነዚህ አውዳሚ የጦር መሳሪያዎች እንዳይጠቀሙ ለመከላከል ወስናለች፡፡.

በጅምላ አጥፊየጦር መሳሪያዎችን በመጠቀም በመላው አለም በሚገኙ የአሜሪካ ዜጐችና ጥቅሞች ላይ የአለም አቀፍ ሽብር ተግባርን የፈፀመ ወይም ለመፈፀም የሞከረ ወይም እንዲፈጸ ም ተባባሪ የሆነ ወይም የረዳ እና የተሳተፈ ማንኛውንም ግለሰብ በቁጥጥር ስር ለማዋል ወይም በሕግ ተጠያቂ ለማድረግ የሚረዳ መረጃን ከሰጡ ሽልማት ሊያገኙ ይችላሉ፡.

ማሳሰቢያ፤ ሁን ተብሎ የሚሰጥ ማንኛውም ሀሰተኛ መረጃ አግባብነት ላላቸው ባለስልጣናት ሪፖርት ይደረጋል፡፡.

እ.ኤ.አ ሐምሌ 15፣ 2006 ላይ ፕሬዝዳንት ቡሽ እና ፕሬዝዳንት ፑቲን የኑክለር አሸባሪነትን ለመዋጋት አለም አቀፍ ጅምር አስተሳሳቢ አፈለቁ። የዚህ ልዩ ጅምር የማፍለቅ ሃሳብ ዓላማ የተደቀነውን አለም አቀፍ የኑክሌር ሽብርተኝነትን አደጋን ለመዋጋት አለም አቀፋዊ አጋርነትን ለማስፋፋትና ለማሳደግ ነው፡፡.