የስኬታማነት ታሪኮች

የወሮታዎች ለፍትህ መርኃ ግብር ዓለም አቀፍ የሽብርተኝነት ጥቃቶችን በመከላከል ወይም በቀደሙት ተግባሮች የተሳተፉትን ለፍትህ በማቅረብ ለረዱት ከ100 በላይ ለሆኑ ሰዎች ከ$150 ሚሊዮን በላይ ከፍሎአል።

መረጃዎን ለመስጠት ፈቃደኛ የሆኑ ልበ ሙሉ ግለሰቦችም የሽብርተኝነት ጥቃቶችን በመከላከልና በማስቀረት ረገድ የራሳቸውን እርዳታ አበርክተዋል፡፡:

  • ፍትህ ለወሮታ (RFJ) በመካከለኛው ምስራቅ የአይሲስ (ISIS) ቁልፍ መሪ ለፍትህ ላመጣው ፍትህ እ.ኤ.አ. በ 2019 የብዙ ሚሊዮኖች ዶላር ክፍያ ፈጽሞአል፡፡
  • የፋርስ ባህረ ሰላጤ ጦርነት በሚካሄድበት ወቅት ከምስራቅ ኤሰያ አገር የተገኘ ጎበዝ መረጃ አቅራቢ ግለሰብ ስለታቀዱ ተከታታይ የሽብር ጥቃቶች መረጃ ሰጥቷል፡፡ አሸባሪዎቹ በወቅቱ ጥቃት ሊፈጽሙባቸው ያቀዷቸውን ኢላማዎች ለይተው በማስቀመጥ አውቶማቲክ የጦር መሳሪያዎችን የእጅ ቦምቦችንና ተቀጣጣይ ፈንጂዎችን አዘጋጅተው ነበር፡፡ ከታቀዱት ጥቃቶች መካከል የመጀመሪያው ከመድረሱ ጊዜ ከ48 ሰዓት በፊት ይህ መረጃ ሰጭ የአሸባሪዎቹን እቅድ ለማኮላሸት በጣም ወሳኝ የሆነውን መረጃ ሰጥቷል፡፡ ጥቃቱ ከሽፎ መረጃ ሰጪው ወጣት ከፍተኛ ወሮታ ተለግሶለት ቤተሰቡ ደህንነቱ ወደ ተረጋገጠ ቦታ እንዲዛወር ተደርጓል፡፡ ግለሰቡ ይህንን መረጃ በመስጠቱ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ህይወት ከሞት አትርፏል፡፡.
  • በሌላ ሁኔታ ደግሞ፣ አንዲት ወጣት ሴት የመንገደኞች ማጓጓዣ አውሮፕላንን በመጥለፍ በውስጡ የነበሩ ተጓዦችን በአሰቃቂ ሁኔታ ስለ ደበደቡ ሰዎች መረጃ ይዛ መጣች፡፡ ” ፍትህ ተፈጻሚ መሆን አለበት” የሚል ጠንካራ ስሜት እንዳደረባት ተናግራለች:: የጠላፊዎቹ መሪ ወደ አሜሪካ እንዲመለስ ተደርጎ በቀረበበት የአውሮፕላን ጠለፋ ወንጀል ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ እስር ቤት ሊገባ ችሏል፡፡ ወጣቷ ሴት ሽብርተኝነትን ለመዋጋት ላደረገችው ጥረት ወሮታዋን አግኝታለች፡፡.
  • በአንድ የውጭ ሀገር ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ተማሪ የሆነች ሌላ ወጣት ሴት በአንድ የአሜሪካ ዲፕሎማት ላይ በጭካኔ ስለ ተፈፀመ የነፍስ ማጥፋት ወንጀል ምስክርነቷን ሰጥታለች፡፡ እሷ በሰጠችው መረጃ ምክንያትም በሁለት ጥቃት ፈጻሚዎች ላይ ፍ/ቤት የእድሜ ልክ እስር ሊወስንባቸው ችሏል፡፡ ተማሪዋና ቤተሰቧ ደህንነቱ አስተማማኝ ወደሆነ ቦታ እንዲዛወሩ ተደርገው ተማሪዋ ከፍተኛ መጠን ያለው የገንዘብ ወሮታ ተሰጥቷታል፡፡.