ስለ ፕሮግራሙ በተመለከተ የተሰጠ አጠቃላይ ቅኝት

የወሮታ ለፍትህ መርኃ ግብር ፣ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የወሮታ ለፍትህ የጸረ ሽብርተኝነት መርኃ ግብር፣ ዓለም አቀፋዊ ሽብርተኝነትን ለመዋጋት የተደነገገው በ1984 ዓ ም የህዝብ ህግ (በ22 U.S.C. § 2708 ኮድ የተሰጠበት) ነው። በአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር በዲፕሎማሲያዊ ደህንነት ቢሮ የሚተዳደረው፣ የወሮታ ለፍትህ መርኃ ግብር ግብ ዓለም አቀፋዊ አሸባሪዎችን ለፍርድ ለማቅረብና በአሜሪካ ሰዎች ወይም ንብረት ላይ ዓለም አቀፋዊ ሽብርተኝነትን መከላከል ነው። በዚህ መርኃ ግብር ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በአሜሪካ ሰዎች ወይም ንብረት ላይ ዓለም አቀፋዊ ሽብርተኝነትን የሚያቅደውን ፣ የሚፈጽመውን፣ የሚረዳውን፣ ወይም የሚሞክረውን ማንኛውም ሰው በተላይ ለማስያዝ ወይም ለማስፈረድ፣ በመጀመሪያ ደረጃ እንደዚያ ዓይነት ድርጊቶች እንዳይፈጸሙ፣ ቁልፍ የሆነውን የሽብርተኝነት መሪን ፣ ወይም መሪው ያለበትን ቦታ፣ የሽብርተኝነት የገንዘብ ምንጭ የሚያደናቅፍ መረጃ ለማግኘት የሚመራውን መረጃ ለሚያቃብል ሰው ወሮታ ሊፈቅድ እንደሚችል ይገልጻል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሽብርተኝነትን ለመወጋት ወይም ዩናይትድ ስቴትስን ሊፈፀሙበት ከሚችሉ የአሸባሪነት ተግባራት ለመከላከል በሚያስተላልፉት ውሳኔ መሰረት ከ25 ሚሊዮን ዶላር በላይ ወሮታ እንዲያበረክቱ ወይም እንዲከፍሉ ስልጣን ሰጥቷቸዋል፡፡- አልቀይዳ

ወሮታ ለፍትሕ ፕሮግራም ከተጠነሰሰበት ከ1976 ዓ.ም. (እንደ አ.አ. ከ1984) ጀምሮ የዩናይትድ እስቴትስ መንግሥት አሸባሪዎችን በቁጥጥር ሥር ለማዋል ወይም በመላው ዓለም ሊፈጸሙ የነበሩ የሸብር ተግባራትን ለማስቀረት እርምጃ ለመውሰድ የሚያበቁ መረጃዎችን ለሰጡ ከ100 ለሚበልጡ ሰዎች ከ$150 ሚሊዮን በላይ ከፍሏል። ፕሮግራሙ በ1985 ዓ.ም. (እንደ አ.አ. በ1993) በዓለም የንግድ ማዕከል ላይ ለደረሰው የቦምብ ጥቃት ተጠያቂ የሆነው ዓለም አቀፍ አሸባሪ ራምዚ ዩሱፍ በቁጥጥር ሥር አንዲውል ጉልህ ሚና ተጫውቷል፡፡

ወሮታ ለፍትህ ፕሮግራምን የሚገዛው ሕግ አላማው በአሜሪካውያን ላይ የሚቃጣ ሽብርን መዋጋት ሲሆን ዩናይትድ ስቴትስ እነዚህን መረጃዎች ዜጎቻቸው በአደጋ ላይ ለሚወድቁ ሌሎች መንግስታት ያካፍላሉ፡፡ እያንዳንዱ መንግስትና እያንዳንዱ ዜጋ አሸባሪዎችን ወደ ፍትህ በማምጣትና የሽብርተኝነት ተግባራትን በመከላከል ረገድ ድርሻ አላቸው፡፡.