ዘየጥ (ዘወትር የሚቀርቡ ጥያቄዎች)

 • ስለ ወሮታ ለፍትህ ፕሮግራም (አር ኤፍ ጄ) የተወሰኑ መረጃዎችን መስጠት ይችላሉ?

  ስለ ወሮታ ለፍትህ ፕሮግራም (አር ኤፍ ጄ) የተወሰኑ መረጃዎችን መስጠት ይችላሉ?

  • የወሮታ ለፍትህ መርኃ ግብር ፣ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የወሮታ ለፍትህ የጸረ ሽብርተኝነት መርኃ ግብር፣ ዓለም አቀፋዊ ሽብርተኝነትን ለመዋጋት የተደነገገው በ1984 ዓ ም የህዝብ ህግ (በ22 U.S.C. § 2708 ኮድ የተሰጠበት) ነው። በአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር በዲፕሎማሲያዊ ደህንነት ቢሮ የሚተዳደረው፣ የወሮታ ለፍትህ መርኃ ግብር ግብ ዓለም አቀፋዊ አሸባሪዎችን ለፍርድ ለማቅረብና በአሜሪካ ሰዎች ወይም ንብረት ላይ ዓለም አቀፋዊ ሽብርተኝነትን መከላከል ነው። በዚህ መርኃ ግብር ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በአሜሪካ ሰዎች ወይም ንብረት ላይ ዓለም አቀፋዊ ሽብርተኝነትን የሚያቅደውን ፣ የሚፈጽመውን፣ የሚረዳውን፣ ወይም የሚሞክረውን ማንኛውም ሰው በተላይ ለማስያዝ ወይም ለማስፈረድ፣ በመጀመሪያ ደረጃ እንደዚያ ዓይነት ድርጊቶች እንዳይፈጸሙ፣ ቁልፍ የሆነውን የሽብርተኝነት መሪን ፣ ወይም መሪው ያለበትን ቦታ፣ የሽብርተኝነት የገንዘብ ምንጭ የሚያደናቅፍ መረጃ ለማግኘት የሚመራውን መረጃ ለሚያቃብል ሰው ወሮታ ሊፈቅድ እንደሚችል ይገልጻል።

   ወለፍ በየወቅቱ የቀረቡ የሽልማት ዝርዝሮችን በሚከተለው ድህረ ገፁ ያሳውቃል፡፡ WWW.rewardsforjustice.net. አብዛኞቹ የወለፍ ወሮታዎች እስከ 5 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ይደርሳሉ፡፡ ይሁን እንጂ የቀረቡት ሽልማቶች ከ1 ሚሊዮን እስከ 25 ሚሊዮን ዶላር ሊደርሱ ይችላሉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪም እንደአግባብነቱ እየታየ አስቀድሞ የተቀመጠ ወሮታ በሌለበት ሁኔታ ወለፍ ወሮታ ሊከፍል ይችላል፡፡.

   ከተጠነሰሰበት ጊዜ ጀምሮ፣ ወለፍ የአለም አቀፍ ሽብርተኝነት ጥቃቶችን ለመከላከል ያስቻሉ ወይም ቀደም ሲል በሽብር ተግባራት ውስጥ የተሳተፉ ሰዎችን ወደ ፍትህ ለማቅረብ የረዱ መረጃዎችን ለሰጡ ከ100 በላይ ግለሰቦች ከ150 ሚሊዮን ዶላር የበለጠ ወሮታ ከፍሏል፡፡

 • ወሮታ ለፍትሕ ምን ያክል ውጤታማ ነው?

  ወሮታ ለፍትሕ ምን ያክል ውጤታማ ነው?

  • ከወለፍ ፕሮግራም ጋር በተገናኘ መረጃ ሰጪዎች በአሜሪካ ጥቅሞች ላይ ሊፈፀሙ ታቅደው የነበሩ ጥቃቶችን ለመከላከል ወይም ለማክሸፍ የረዱ እና በአለምቀፍ ደረጃ በአስከፊነት በታወቁ አሸባሪዎች ላይ መረጃ ሰጥተዋል፡፡ እነዚህ ጥረቶች ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ንፁህ ሰዎችን ህይወት አድነዋል፡፡.

   ለምሳሌ ኢራቅ ውስጥ ለኡዴይና ለቋይ ሁሴን የቀረቡ ወሮታዎች ለሕዝብ ግልጽ ከተደረጉ ከ18 ቀናት በኋላ የመረጃ ምንጭ ቀርቦ ስለሚገኝበት ቦታ መረጃ ሰጥቷል፡፡ ሌላ በጣም ታዋቂ ስኬት ያጋጠመው ደግሞ በተገኘው ባቀረበው ሽልማት ምክንያት በቀረበው መረጃ እ.አ.አ. 1993 ውስጥ በአለም አቀፉ የንግድ ማዕከል ላይ የቦንብ ጥቃት ካደረሱት መካከል አንዱ የሆነው ራምዚ ዩሱፍ እ.አ.አ. 1995 ውስጥ በቁጥጥር ስር መዋሉ ነው፡፡.

 • የሚለገሱ ወሮታዎችን እንዴት ታሳውቃላችሁሉ?

  የሚለገሱ ወሮታዎችን እንዴት ታሳውቃላችሁሉ?

  • ከወለፍ ድህረ ገጽ በተጨማሪ በዩናይትድ ስቴትስ ላይ ለተፈፀሙ/ ለሚፈፀሙ የሽብር ጥቃቶች ተጠያቂ የሆኑ ሰዎችን ወደ ፍትህ ለማቅረብ ፖስተሮ ችን፣ ተቀራራቢ ንድፎችን፣ የክፍያ ማስታወቂያዎችን፣ በራዲዮና በጋዜጦች፣ በኢንተርኔት እና ሌሎች አግባብነት ባላቸው መንገዶች እንጠቀማለን፡፡.

 • ስለ ወሮታ ልገሳዎች ምን አይነት መረጃዎችን ይፋ ታደርጋላችሁ?

  ስለ ወሮታ ልገሳዎች ምን አይነት መረጃዎችን ይፋ ታደርጋላችሁ?

  • ይህንን ፕሮግራም የተለየ የሚያደርገው ለወሮታ ለምናካሄደው ውድድር የሚገኘው ምላሽ በጥብቅ ሚስጥር የሚጠበቅ መሆኑ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ትልቁ ቁም ነገር ወሮታ ያገኙትን ሰዎች ስም ግልጽ የማናደርግ ከመሆናችን በተጨማሪ አብዛኛውን ጊዜ ሽልማት መሳጠቱንም አናሳውቅም፡፡ ከፍ ያለ ግለ ታሪክ ያላቸውን ተሸላሚዎች በሚመለከት የሽልማት ክፍያ መፈፀሙን በግልጽ የምናሳውቅ ቢሆንም የተገኘውን መረጃ ግን ይፋ አናደርግም፡፡.

 • ስለያንዳንዱ የወሮታ ክፍያዎች የተወሰኑ ዝርዝር መረጃዎችን መስጠት ትችላለችሁ?

  ስለያንዳንዱ የወሮታ ክፍያዎች የተወሰኑ ዝርዝር መረጃዎችን መስጠት ትችላለችሁ?

  • እስካሁን ለአንድ ግለሰብ የተከፈለ ከፍተኛ የወሮታ ገንዘብ መጠን 30 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ሲሆን ከዚህ ተሸላሚ በተገኘ መረጃ ኡደይ እና ቋዘይ ሁሴንን ለመያዝ ተችሏል፡፡.

   እስከአሁን አራት በግልፅ የተደረጉ የወሮፍ የሽልማት ስነ ሥርዓቶች በፊሊፒንስ ተከናውነዋል፡፡ ከነዚህም መሃከል በቅርብ የተደረገው የሽልማት ሥነ-ሥርዓት እ.አ.አ. በሰኔ 7፣ 2007 የተደረገው ሲሆን በዚህ ሥነ ሥርዓት የተደረገው ጠቅላላ የገንዘብ መጠንም 10 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ነው፡፡ ይህ የወሮታ ገንዘብ መጠንም በፊሊፒንስ ፕሮግራሙ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ በፊሊፒንስ ውስጥ የተሰጠ ከፍተኛ የወለፍ ክፍያ መጠን ነው።.

 • በአጠቃላይ ዝርዝር መረጃዎችን ካልሰጣችሁ ወሮታዎች በትክክል መከፈላቸውን እንዴት ማረጋገጥ እንችላለን?

  በአጠቃላይ ዝርዝር መረጃዎችን ካልሰጣችሁ ወሮታዎች በትክክል መከፈላቸውን እንዴት ማረጋገጥ እንችላለን?

  • ከፍ ሲል እንደተገለጸው፣ ከፍተኛ ግለ ታሪክ ላላቸው ግለሰቦች የተደረገ ሽልማትን በሚመለከት ወለፍ አልፎ አልፎ የተወሰነ ማስታወቂያ ያደርጋል፡፡ ሽልማት ከተደረገ በኋላም ለአሜሪካ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዘገባ ይቀርባል፡፡.

 • ሽልማት የሚያስገኘው ምንድን ነው? የምትፈልጉት ምን አይነት መረጃ ነው?

  ሽልማት የሚያስገኘው ምንድን ነው? የምትፈልጉት ምን አይነት መረጃ ነው?

  • Anyone who provides actionable information that will either help us prevent or favorably resolve acts of international terrorism against the U.S. anywhere in the world may potentially be eligible for a reward.
   If, for example, a terrorist involved in either the planning or execution of an attack against U.S. persons and/or property is arrested or convicted as a result of information provided by a source, that source may be eligible for a reward.
   In addition, anyone with information regarding the identification or location of a key leader in an international terrorist organization may be eligible for a reward. Rewards may also be paid for information about an individual or organization that is trafficking drugs to finance acts of international terrorism or to raise money to sustain or support a terrorist organization.
   However, under the law that governs the program, U.S., state, local, and foreign government employees are generally not eligible for a reward if they provide information obtained in the performance of their official duties.

   በአሜሪካ ላይ ሊቃጣ የሚችለውን አለም አቀፍ ሽብርተኝነትን ለመከላከል ወይም በጥሩ ሁኔታ መፍትሄ ለመስጠት የሚያግዘን ተግባራዊ መረጃ ለሰጠን በየትኛውም አለም አቀፍ ክፍል የሚገኝ ግለሰብ እጬ ተሸላሚ ሊሆን ይችላል፡፡.

   ለምሳሌ፣ በአሜሪካ ዜጎች ወይም/እንዲሁም ንብረት ላይ ሊደረግ በሚችል ጥቃት እቅድ በማውጣት ላይ ወይም በተካሄደ ጥቃት ውስጥ የተሳታፊ አሸባሪ የመረጃ ምንጭ በሆነ ግለሰብ አማካኝነት ከተያዘ ወይም ከተፈረደበት መረጃውን የሰጠው ግለሰብ ለሽልማት እጩ መሆን ይችላል፡፡.

   ከዚህ በተጨማሪ፣ የአለም አቀፍ የሽብርተኝነት ተቋም መሪ ማንነትን ወይም አድራሻን ለመለየት የሚያግዝ መረጃ የሰጠ ማንኛወም ሰው ለዚህ ሽልማት እጩ መሆን ይችላል፡፡ የአለም አቀፍ ሽብርተኝነትን በገንዘብ ለማገዝ ወይም የሽብርተነኝነትን ተቋም ለማገዝ ወይም ተግባሩን በቀጣይነት ለማከናወን ገንዘብ የሚያዋጣ ወይም አደንዛዥ እፆችን የሚያዘዋውር ግለሰብን ወይም ድርጅትን የሚመለከት መረጃ የሰጠ ግለሰብ ሽልማት ሊሰጠው ይችላል፡፡.

   ነገር ግን ይህንን ፕሮግራም በሚገዛው ሕግ መሰረት የአሜሪካ የፌደራል መንግስት መስሪያ ቤት፣ የአሜሪካ የክልል መንግስታት መስሪያ ቤት፣ የወረዳ መስሪያ ቤት እና የውጭ ሃገራት የመንግስት ሰራተኛ በስራው ምክንያት ያገኘውን መረጃ በመስጠቱ ለዚህ ሽልማት እጩ መሆን አይችልም፡፡.

 • መረጃ ሰጪው በሽብር ዙሪያ መረጃ በመስጠቱ ህይወቱ አደጋ ላይ የሚወድቅ ከሆነና ህይወቱ አደጋ ላይ መውደቁን ካወቀስ? ወለፍ ጥበቃ ሊያደርግለት ይችላልን?

  መረጃ ሰጪው በሽብር ዙሪያ መረጃ በመስጠቱ ህይወቱ አደጋ ላይ የሚወድቅ ከሆነና ህይወቱ አደጋ ላይ መውደቁን ካወቀስ? ወለፍ ጥበቃ ሊያደርግለት ይችላልን?

  • ከፍ ብሎ እንደተገለፀው፣ ምስጢር ጥበቃ የወለፍ ፕሮግራም የመሰረተ ድንጋይ ነው፡፡ በሽልማቱ ጥሪ መሰረት መረጃን የሰጠ ግለሰብ ወይም/እና በሰጠው መረጃ መሰረት ሽልማት ያገኘን ግለሰብ ማንነት በሚመለከት ወለፍ ሚስጢራዊነቱን በጥብቅ ይጠብቃል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ እንደየ ጉዳዩ ባህሪ እየታየ ነው የመረጃ ምንጭ የሆነውን ግለሰብ እና ቤተሰቦቹን ወደ ሌላ ቦታ የማዛወር ተግባር የሚካሄደው፡፡.

 • ግለሰቦች ክፍያቸውን የሚያገኙት እንዴት ነው?

  ግለሰቦች ክፍያቸውን የሚያገኙት እንዴት ነው?

  • Each reward nomination is considered on a case-by-case basis. The process for paying a reward is as follows:
   Either a U.S. investigating agency, such as the Department of Defense or the FBI, or a U.S. embassy abroad, must first nominate a person for a reward. An interagency committee then carefully evaluates the information. If the Interagency Rewards Committee believes an individual is eligible for a reward, it recommends that the Secretary of State approve a reward.
   The recommendation of the Committee, however, is not binding. The Secretary of State has complete discretion over whether or not to authorize a given reward, and can change the amount of the reward, within the terms of the law.
   If there is a federal criminal jurisdiction in the matter, the Secretary requests the concurrence of the Attorney General before paying the reward.

   የእያንዳንዱን ሽልማት እጩ ለመመልመል ሁኔታ ከግምት ውስጥ ይገባል፡፡ ክፍያውን ለማከናወን የሚደረገው ሂደት እንደሚከተለው ነው፤

   የአሜሪካ የምርመራ ድርጅት የሆነ ማለትም እንደ መከላከያ መ/ቤት፣ ወይም የፌደራል ምርመራ ቢሮ፣ ወይም በውጭ ሃገር የሚገኝ የአሜሪካ ኢምባሲ መጀመሪያ ሽልማቱን ሊያገኙ የሚችሉ ሰዎችን መመልመል አለበት፡፡ በመቀጠልም የድርጅቶች ጥምር ኮሚቴ መረጃውን በጥንቃቄ ይመረምረዋል፡፡ የድርጅቶች ጥምር የሽልማት ኮሚቴ መረጃ የሰጠውን ግለሰብ ለሽልማቱ ብቁ ነው ብሎ ካመነ የውሳኔ ሃሳቡ እንዲፀድቅ ለአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያቀርባል፡፡.

   ይሁን እጂ፣ የዚህ ኮሚቴ የውሳኔ ሃሳብ አሰገዳጅነት የለውም፡፡ በሕጉ መሰረት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሽልማቱን ለማጽደቅ ወይም ላለማፅደቅ እና የሽልማቱን መጠን ለመቀየር የሚያስችል ሙሉ ስልጣን አለው፡፡.

   የፌደራሉ መንግስት ወንጀሉን ለማየት የሚያስችል የሥልጣን ክልል ካለ፣ የሽልማት ክፍያ ከመከናወኑ በፊት የሃገሪቱ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ በጉዳዩ ሲሆን እንዲገልጽ የውጭ ጉዳይ ሚነስትሩ ይጠይቃል፡፡.

 • የወሮታ ክፍያ መጠን የሚወሰነው እንዴት ነው?

  የወሮታ ክፍያ መጠን የሚወሰነው እንዴት ነው?

  • የወሮታ መጠን የሚወሰነው በርከት ባሉ ሁኔታ¬ች ላይ ተመስርቶ ሲሆን ሌሎች ጭብጦችን ከግምት ውስጥ በማስገባትም ጭምር ይሆናል፡፡ – በአሜሪካ ዜጋ ወይም ንብረት ላይ ከአሸባሪ የሚሰነዘር የአደጋው ወይም የጉዳቱ መጠን፣ የተሰጠው መረጃ ፋይዳ፣ መረጃውን በሰጠው ግለሰብ እና ቤተሰቡ ላይ ሊደርስ የሚችለውን አደጋ እና በምርመራ ወይም በፍርድ ሂደቱ ላይ የመረጃ ሰጪው የትብብር ደረጃን ያጠቃልላል፡፡.

 • ወለገ አንድን ሰው ከወሮታ ለፍትህ ዝርዝር ሰርዞ ያውቃል? እንደዚያ ከሆነ፣ማን እና ለምን?

  ወለገ አንድን ሰው ከወሮታ ለፍትህ ዝርዝር ሰርዞ ያውቃል? እንደዚያ ከሆነ፣ማን እና ለምን?

  • አዎን፣ ወሮታ ለፍትህ መርኃ ግብር በዓመታት ውስጥ፣በይቱላ ሜሹድ፣በባሊ ቦምቡ አፈንጂው ዱልማቲን፣ኡሳማ ቢን ላድን፣አትያ አብድ አል ራሃማን እና ፋዙል አብዱላ መሀመድን ጨምሮ የተለያዩ ተጠርጣሪዎችን ከዝርዝሩ ሰርዞአል። ተጠርጣሪዎቹ በሕግ አስከባሪ ወይም በደህንነት ኃይሎች ሲታሰሩ ወይም በህጋዊ ባለሥልጣን ምንጮች መሞቱ ሲረጋገጥ ከወሮታ ለፍትህ ዝርዝር በተለያዩ ምክንያቶች ሊሰረዙ ይችላሉ።

 • ወሮታዎች ለፍትህ ሂሳብን በተመለከተ ዝርዝር መረጃዎችን ማቅረብ ትችላላችሁ?

  ወሮታዎች ለፍትህ ሂሳብን በተመለከተ ዝርዝር መረጃዎችን ማቅረብ ትችላላችሁ?

  • ወሮታ ለፍትህ ገንዘብ (ወለገ) ማለት መንግስታዊ ያልሆነ ለትርፍ ያልቆመ 501 (ሲ) (3) የበጎ አድራጊ ድርጅት ሲሆነ የአሜሪካ የወሮታ መስሪያ ቤት ከፍትህ ፕሮግራም ጋር ባለው ብቸኛ ግንኙነት በአሜሪካ አገር ውስጥ እና በውጭ ሃገር የሚንቀሳቀሱ አሸባሪዎችን ለመለየትና ለመያዝ የሚያግዝ የግል አስተዋጽኦ /እገዛ የሚያደርግና የሚጠይቅ ነው፡፡ ወሮታ ለፍትህ ገንዘብ በአሜሪካ ግለሰቦች የተቋቋመ እና የሚተዳደር የበጎ አድራጎት ድርጅት ነበረ፡፡ ወሮታ ለፍትህ ገንዘብ የተመሠረተው ግለሰቦች በሆኑ የአሜሪካ ዜጎች ነው። በመስከረም 11 ቀን በአሜሪካ ላይ የሽብር አደጋ ከደረሰ በኋላ እነዚህ ግለሰቦች ወደ አሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በመቅረብ በስጦታ ከሕዝብ ገንዘብ በማዋጣት ወለገን ለማገዝ እንዲፈቀድላቸው ጠየቁ፡፡ [ማሳሰቢያ፣በዚህ ጽሁፍ ውስጥ የተጠቀሱ ቀናትና ዓ ም በተላይ ካልተጠቀሱ በስተቀር የተገለጹት እንደ ኤውሮፓውያን አቆጣጠር ነው]። እኛም ሃሳቡን ገምግመን የወለገን ጥራት ደገፍን። ከመስከረም 11 ቀን በኋላ ለዓመታት ድጋፍ ከሰጠ በኋላ ንዋዩ በነሀሴ 2008 ዓ ም ፈረሰ።

 • ወሮታ በመለገስ በማቅረባችሁ ሽልማት አሳዳጆችን ማበረታታችሁ አይሆንም?

  ወሮታ በመለገስ በማቅረባችሁ ሽልማት አሳዳጆችን ማበረታታችሁ አይሆንም?

  • ግለሰቦች ጉርሻን ለማሳደድ ሲሉ አሸባሪዎችን ለመያዝ ሙከራ እንዲያደርጉ አናበረታታም:: ከዚህ ይልቅ ወለፍ የመንግስት አካላት የአሸባሪዎችን አድራሻ ወይም አሸባሪዎችን ለመያዝ የሚያስችላቸውን መረጃ ለሚሰጡ ግለሰቦች ወሮታ ይለግሳል፡፡.

 • መረጃ መስጠት ብፈልግ የምገናኘው ከማን ጋር ነው?

  መረጃ መስጠት ብፈልግ የምገናኘው ከማን ጋር ነው?

  • People with information should contact the Regional Security Office at the nearest U.S. embassy or consulate, the FBI, or use the following contact information:
   Mailing address: RFJ, Washington D.C. 20522-0303, USA Toll-free number: 1-800-US-REWARDS Email: [email protected]

   መረጃ መስጠት የሚፈልጉ ግለሰቦች በአሜሪካ ኢምባሲ አቅራቢያ ወደ ሚገኘው የክፍለ አህጉራዊ የውጭ ጉዳይ ጽ/ቤት ወይም ወደ ፌቢአይ በመቅረብ መረጃውን መስጠት የሚችሉ መሆናቸውን ወይም ከዚህ ቀጥሎ በተዘረዘሩት አማካኝነት ያገኙትን መረጃ መስጠት ይችላሉ፡፡:

   በፖስታ ሳጥን ቁጥር አድራሻ: RFJ, Washington D.C. 20522-0303, U.S.A በስልክ ቁጥር 1-800-US-REWARDS Email: [email protected]

 • በአቅርቦቴ ወይም በማሳትማቸው ነገሮች ማቴሪያሎችን (ምስሎችን) ከእናንተ ድህረ ገጽ ለመጠቀም እንዲፈቀድልኝ እኔ እጠይቃለሁ፡፡

  በአቅርቦቴ ወይም በማሳትማቸው ነገሮች ማቴሪያሎችን (ምስሎችን) ከእናንተ ድህረ ገጽ ለመጠቀም እንዲፈቀድልኝ እኔ እጠይቃለሁ፡፡

  •  

   የባለቤትነት መብት የሚል በግልጽ ካልተቀመጠ በስተቀር በዚህ ድህረ ገጽ የሚገኝ መረጃ ከወለፍ ግልጽ ከመሆኑም በተጨማሪ ከወለፍ ፈቃድ ውጪ ሊባዛ፣ ሊታተም ወይም በሌላ መንገድ ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል፡፡ ከዚህ ድህረ ገጽ የተገኘ መረጃ ምንጩ ወለፍ መሆኑን እንዲገልፁ እና የፎቶ ምስጋና ወይም የደራሲውን ስምና ማዕረጎች ይበተመሳሳይ መንገድ ለፎቶግራፉ ወይም ለደራሲው ወይም ወለፍ እውቅና እንዲሰጡ እንጠይቅዎታለን፡፡.

   ነገር ግን በፎቶግራፍ ፣በቅርጽ ወይም በሌላ ማቴሪይል ላይ የባለቤትነት መብት የሚል በግልጽ ከተቀመጠ እነዚህን ማቴሪይሎች ከመጠቀምዎ በፊት ከደራሲው ፈቃድ ማግኘት አለብዎት። የወንጀል መቅጫ ሕግ 18 ዩ ኤስ ሲ 713፣ በማንኛውም ሁኔታ የአሜሪካን ታላቅ ማህተም መጠቀም የማይቻል ስለሆነ በማንኛውም ሁኔታ ታላቅ ማህተምን ከመጠቀም በፊት አማካሪዎን እንዲያማክሩ ሃሳብ እናካፍልዎታለን፡፡.