የሚፈለጉ
ፍትህ የሚያመጣ መረጃ…

አብዱላህ አህመድ አብዱላህ

እስከ $10 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚደርስ ወሮታ

አብዱላህ የአልቃይዳ አንጋፋ መሪ እና “የመጅሊስ አል- ሹራ” ፣ የአልቃይዳ አመራር ምክር ቤት አባል ነው ፡፡አብዱላህ ልምድ ያለው የአልቃይዳ የገንዘብ ሹም ፣ የሚያመቻች፣ እና የድርጊት አቃጅ ነው፡፡

አብዱላህ፣ በደሬሳለም፣ ታንዛኒያ እና በናይሮቢ፣ ኬንያ፣ በነሀሴ 7 ቀን 1998 ፣ በአሜሪካ ኤምባሲዎች ላይ ለደረሱት የቦምብ ጥቃቶች በነበረው ሚና፣ በታህሳስ 1998 በፌዴራል ጠቅላይ የፍርድ ጁሪ ክስ ተመስርቶበታል፡፡ ጥቃቶቹ 224 ሲቪሎችን ገድሎ ከ5,000 በላይ የሆኑትን ሌሎችን አቁስሎአል፡፡

በ1990ዎቹ፣ አብዱላህ ለአልቃይዳ ተዋጊዎች እንዲሁም በ Operation Restore Hope ወቅት ከአሜሪካ የጦር ሃይሎች ጋር ለተዋጉት ለሶማሊያ የጎሳ ሰዎች የውትድርና ሥልጠና ሰጥቶአል፡፡ እርሱም ከ1996-1998፣ በአፍጋኒስታን ፣ የአልቃይዳ የሥልጠና ካምፖችን አካሄዶአል፡፡

በኤምባሲው ከደረሱት የቦምብ ጥቃቶች በኋላ፣ አብዱላህ በ ኢራን Islamic Revolutionary Guard Corps (IRGC) ጥበቃ ወደ ኢራን ሄዶአል፡፡ በ2003 የኢራን ባለሥልጣናት እርሱንና ሌሎች የአልቃይዳ መሪዎችን የቤት ውስጥ እስረኞች አድርጎአቸዋል፡፡ በመስከረም 2015፣ በየመኑ አልቃይዳ በታገተው የኢራን ዲፕሎማት ልዋጭ አብዱላህና ሌሎች የአልቃይዳ መሪዎች ከኢራን እስር ቤት ተለቀቁ፡፡

የተጨማሪ ፎቶ

የ--- ፎቶ አብዱላህ አህመድ አብዱላህ
English AAA and SaA PDF